-ሰሜን ኢትዮጵያ ዉስጥ ዳግም ጦርነት ይጫራል ብለዉ በመሥጋት ከየቀያቸዉ የሸሹ የአለማጣ፣ የኮረምና የአካባቢዉ ነዋሪዎች የሰብአዊ ርዳታ እንዲደረግላቸዉ ጠየቁ።ከ60ሺሕ የሚበልጡት ነዋሪዎች ከየቀያቸዉ የሸሹት ከሁለት ሳምንት በፊት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አካባቢዉን ልቅቆ በመዉጣቱ ነዉ። -የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ኃይላት የገጠሙት ጠብ በአዲሲቱ አፍሪቃዊት ሐገር የከፋ ደም መፋሰስ ሊያስከትል እንደሚችል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስጠነቀቀ።-የኢራን እስላማዊ አብዮተኞች ሥልጣን የያዙበት 47ኛ ዓመት በጦርነት ሥጋት፣ በዛቻና ተቃዋሞ መሐል ዛሬ ተከብሮ ዋለ።