የሶማሊያ ፌድራል መንግሥት እና የደቡብ ምዕራብ ሶማሊያ ግዛት በመካከላቸው የተፈጠረውን ውጥረት ከማባባስ እንዲቆጠቡ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ማሕሙድ አሊ ይሱፍ አሳሰቡ። አሜሪካና እስራኤል ከኢራን የሚያካሒዱት ውጊያ የሚቆምበት ሁኔታ ላይ ለመወያየት የቀጠናው ቁልፍ ሀገራት ከፍተኛ ዲፕሎማቶች በፓኪስታን ተሰበሰቡ። ጦርነቱ ዓለም አቀፍ ሕግ እንደሚጥስ ቡንደስታግ ተብሎ የሚጠራው የጀርመን ምክር ቤት የምርምር አገልግሎት ይፋ ያደረገው ሪፖርት አሳየ። በአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕና ፖሊሲዎቻቸውን ለመቃወም በተለያዩ ከተሞች በተካሔዱ ሰልፎች ቢያንስ 8 ሚሊዮን ሰዎች ተሳትፈዋል ተብሎ እንደሚገመት አዘጋጆቹ አስታወቁ።