የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን የመጀመሪያውን የሰነደ ሙዓለ-ንዋይ አማካሪነት ፈቃድ ለዲሎይት ሰጠ።የጋምቤላ ክልል ችግር “እየተባባሰ እንዲሔድ የማድረግ ዝንባሌ” እንዳለ የክልሉ መንግሥት አስጠነቀቀ።ባሲሩ ዲዮማይ ፋይ የሴኔጋል ፕሬዝደንት ሆነው ማክሰኞ ቃለ-መሐላ ሊፈጽሙ ነው። ደቡብ ሱዳን በጎረቤቷ ሱዳን በበረታው ጦርነት ሳቢያ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦዎች በመዘጋታቸው የኤኮኖሚ እና የፖለቲካ ቀውስ እንደሚያሰጋት ባለሙያዎች አስጠነቀቁ። በሰርቢያ ዋና ከተማ ቤልግሬድ በመካሔድ ላይ በሚገኘው የዓለም ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና በወጣት ሴቶች የ6 ኪሎ ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውን አትሌቶች አሸነፉ።