የዓለም ዜና

DW Amharic የመጋቢት 28 ቀን 2016 የዓለም ዜና


Listen Later

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት ደጋፊዎች አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች ሠልፍ አደረጉ። በአማራ ክልል የደብረ ብርሀን እና ደሴ ከተሞችን የሚያገናኘው ዋና አውራ ጎዳና ከዛሬ ጀምሮ ለመንገደኞች ክፍት እንደሆነ የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር አስታወቀ። ሐማስ የግብጽ አደራዳሪዎች ባቀረቡት ግብዣ ነገ እሁድ ለሚካሔደው የተኩስ አቁም ንግግር ልዑካኑን ወደ ካይሮ መላኩን አስታወቀ። ሩሲያ በዩክሬን ኻርካይቭ ከተማ በሚሳይሎች በፈጸመችው ድብደባ ስድስት ሰዎች ተገደሉ። በሶርያ ዳራ ግዛት በተከሰተ ፍንዳታ ሰባት ሕጻናት ተገደሉ። በፕራግ የግማሽ ማራቶን የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ ጌጤ ዓለማየሁ አሸነፈች።
...more
View all episodesView all episodes
Download on the App Store

የዓለም ዜናBy DW