በአማራ ክልል ፍኖተ ሰላም ከተማ ገበያ መሀል ባለፈው ቅዳሜ በተከሰተ ፍንዳታ 32 ሰዎች መቁሰላቸውን የምዕራብ ጎጃም ዞን አስተዳዳሪ ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ። በፍንዳታው ጉዳት የደረሰባቸው አብዛኞቹ ለገበያ ከገጠር ወደ ፍኖተ ሰላም ከተማ የተጓዙ እናቶች እንደሆኑ አቶ እድሜዓለም አንተነህ ገልጸዋል። በኦሮሚያ ክልል የበረታውን ግጭት እና የመንግሥት ጥሪ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት ደጋፊዎች ሰልፍ እና የተቃዋሚዎችን ትችት እንዲሁም የሐዋሳ ሐይቅ የገጠመውን የብክለት ሥጋት የተመለከቱ ዘገባዎች በዜና መጽሔት ተካተዋል።