Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ... more
FAQs about ዜና መጽሔት:How many episodes does ዜና መጽሔት have?The podcast currently has 1,733 episodes available.
September 19, 2025የመስከረም 9 ቀን 2018 የዜና መፅሔትየዓለም ዜና ቀዳሚው ዝግጅታችን ነው። ዜናውን የሚከተለው የዜና መጽሔት ስለኢትዮጵያ የወደብ ጥያቄ የዓለም አቀፍ ሕግ ምን ይላል? በሚል ርዕስ የተጠናቀረውን ዘገባ ያስቀድማል ከባድ ዝናብ በዋግኽምራ በሰብል ላይ ባለደረሰው ጉዳት ላይ የሚያተኩረው ዘገባም አለን።...more9minPlay
September 17, 2025የመስከረም 7 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔትየዜና መጽሔት አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ መቀጠሏ፤ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች በደቡባዊ ትግራይ ዞንና በሌሎች አካባቢዎች የመብት ጥሰት ተፈጽሟል ማለታቸው፤ በእሥር ላይ የሚገኙት አቶ ክርስቲያን ታደለ ሕመም እንደጠናባቸው መገለጹ፤ ነዋሪዎች እንዲፈናቀሉ ያስገደደው አዲስ አበባ ላይ የተከሰው የመሬት መንሸራተት እንዲሁም የአረብ ሃገራት መንግሥታት አስቸኳይ ጉባኤ ውሳኔና አንድምታውን የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል።...more22minPlay
September 16, 2025የመስከረም 6 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔትኢትዮጵያ ዉስጥ ሰላም ሥለሚሰፍንበት ሁኔታ የሚነጋገር ጉባኤ አዲስ አበባ ዉስጥ መጀመሩንአማራ ክልል የሚደረገዉ ግጭት የመማር-ማስተማሩን ሒደት አሁንም እያወከዉ መሆንኑ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢሾፍቱ አጠገብ ሊያስገነባ ሥላቀደዉ ግዙፍ አዉሮፕላን ማረፊያ የተነጋገረ ስብሰባ...more15minPlay
September 15, 2025የመስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔትበዜና መጽሔት ጥንቅራችን፤ ህዝባዊ ሓርነት ትግራይ ህወሓት በፌደራል መንግሥት ላይ የሰነዘረዉ ክስግዕዝ ቋንቋ በአማራ ክልል ስርአተ ትምህርት ዉስጥ መካተቱ ያስነሳዉ ተቃዉሞ ኢትዮጵያ እና ኬኒያ ድንበር ላይ የሚታዩ ግጭቶችን ለመፍታት መስማማታቸዉ ርዕሶችን በስፋት እንዳስሳለን።እንዲሁም ለትምህርት ጥራት ፈተና መፍትሄው የቱ ጋር ነው? የተሰኙት ርዕሶች ይተነተናሉ።...more16minPlay
September 12, 2025የመስከረም 2 ቀን 2018 ዓ.ም የዜና መፅሄትበዛሬው የዜና መጽሄት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በቀሩት 5 የሥራ ወራት ስራውን አከናዎኖ ይጨርስ ይሆን?«ኢትዮጵያ የባህር በር ማግኘት አለባት » ሲል በትግራይ የሚንቀሳቀሰዉ ተቃዋሚዉ ፓርቲ - ትንሳኤ ሰብዓ እንደርታ የመንግሥትን አቋም መደገፉን፤የምክክር ኮሚሽንኑ የሰሜን አሜሪካ ውይይት እና የሕግ ባለሙያ አስተያየት እንዲሁም ነገ ቶክዮ ላይ የሚጀምረዉ 20ኛዉ የዓለም የአትሌቲክስ ሻንፒዮና የሚዳስሱ ርዕሶችን አካቷል።...more16minPlay
September 11, 2025የመስከረም 1 ቀን 2018 ልዩ የበዓል ዝግጅትዓለም ዜና ቀጥሎ በሚቀርበዉ ልዩ የአዲስ አመት ዝግጅታችን፤ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች አዲስ ዓመትን አስመልክቶ የደረሱንን ዘገባዎች እናደምጣለን። በዩናይትድ ስቴትስ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ከአገር ቤት ርቀዉ የአዲሱን ዓመት እንዴት እያከበሩት ነዉ፤ ዘገባ ይኖረናል። --እነዚህን ዘገባዎቻችን በሙዚቃ እያዋዘን በፊስቡክ የቀጥታ ስርጭት የሚከታተሉንን የዶቼ ቬለ ቤተሰቦች አስተያየቶችን በቀጥታ ስርጭት እናስደምጣለን...more26minPlay
September 10, 2025የጳጉሜ 5 ቀን 2017 ዓ.ም የዜና መፅሄትDW Amharic- የዛሬው የዜና መፅሔት ጥንቅራችን፣-የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ምርቃት፣ የወደፊት አጠቃቀምና አስተዳደርን የተመለከተ ፤በአዲሱ ዓመት ዋዜማ የተፈናቃዮች ኑሮንና ሸመታን የሚዳስሱ ከደ,ሴና አሶሳ ሁለት ዘገባዎችን፣ በምዕራብ ወለጋ ዉስጥ የተዛመተዉ የወባ በሽታ ሰዎች መግደልና ማሳመሙን የሚመለከቱ ዘገባዎችን አካቷል።...more21minPlay
September 09, 2025የጳጉሜ 4 ቀን 2017 ዓ/ም የዜና መጽሔትበተለያየ ጎራ የተሰለፉ ኢትዮጵያውን በሙሉ ልብ እንደሚስማሙበት የሚናገሩለት ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ መሠረቱ በተጣለ በ14ኛ ዓመቱ በዛሬው ዕለት በይፋ ተመርቋል። በገንዘባችሁ፤ በሙያና ላባችሁ የየበኩላችሁን አስተዋጽኦ ላደረጋችሁ ሁሉ እንኳን ደስ ያላችሁ! ዛሬ የግድቡን ምርቃት ምክንያት በማድረግ የዜና መጽሔት ትኩረቱን በዚህ ላይ አድርጓል፤ የሕዝብ አስተያየትንም አካተናል፤ የታላቁ ኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስከያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮንም አነጋግረናል።...more21minPlay
September 08, 2025የጳጉሜ 3 ቀን 2017 ዓ.ም. የዜና መጽሔትበዛሬው የዜና መጽሔትበከባባቢ አየር ለውጥ ላይ የሚመክረው በአዲስ አበባ በመካሔድ ላይ የሚገኘው የአፍሪካውያን ሁለተኛ ጉባኤ የኢትዮጵያ የባሕር በር ፍለጋ፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት “የሚታይ የጦርነት ደመና አለ” ማለታቸው እንዲሁም በአማራ ክልል በወጣት ሴቶች የሚከበሩት አሸንድዬ እና ሻደይ በዓላትን የተመለከቱ ዘገባዎች ይቀርባሉ።...more17minPlay
FAQs about ዜና መጽሔት:How many episodes does ዜና መጽሔት have?The podcast currently has 1,733 episodes available.