Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ... more
FAQs about ዜና መጽሔት:How many episodes does ዜና መጽሔት have?The podcast currently has 1,735 episodes available.
August 12, 2025የነሐሴ 6 ቀን 2017ዓ/ም የዜና መጽሄትDW Amharic-የዛሬው የዜና መፅሔት፣ኦሮሚያ ክልል የመንገደኞች እገታ መቀጠሉን፣ አማራ ክልል በተለይ ደቡብ ወሎ ዞን የሰፈሩ ተፈናቃዮች ለረሐብ መጋለጣቸዉን፣ ትግራይ ክልል የሚደረገዉ ሕገ ወጥ የወርቅ ማዕድን ቁፋሮ ያደረሰዉ ጉዳት፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽንና የሲቪክ ድርጅቶች ረቂቅ ሕግ፣ የዩክሬን ጦርት፣የአሜሪካና የሩሲያ መሪዎች የዉይይት ቀጠሮና የአዉሮፖችን ጭንቀት የሚቃኝ ዝግጅት ተጠናቅሮበታል።...more21minPlay
August 11, 2025የነሐሴ 5 ቀን 2017 የዜና ፅሔትበትግራይ ክልል ኃይሎችና ራሱን ከትግራይ ኃይሎች ነጥሎ በአፋር ይንቀሳቀሳል በተባለው ቡድን መካከል ተነሳ የተባለው ግጭት ፣ ካለፈው ሐሙስ አንስቶ የህዝብ የመጓጓዣ አገልግሎት መስጫዎች መንቀሳቀስ ማቆማቸው በጎጃም አካባቢዎች ያስከተላቸው ችግሮች ፣ብልጽግና ፓርቲ ባለፈው ሳምንት ያወጣው መግለጫና የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስተያየት እንዲሁም ፣ ነዳጅ በውድ ዋጋ ለመግዛት ተገደናል የሚሉ ሾፌሮችና የመኪና ባለቤቶች ሮሮ በዛሬው የዜና መጽሔት ዝግጅታችን የሚያስቃኘን ጉዳዮች ናቸው።...more18minPlay
August 08, 2025የነሐሴ 2 ቀን 2017 የዜና መፅሔትየፖለቲካ ፓርቲዎች ስብስብ መንግሥትን በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መንገድ እንዲቀይሩ ጥሪ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከትግራይ ክልል 60 ሺህ ወጣቶች መሰደዳቸው፤ በያዝነው ነሐሴ ወር ከመደበኛ በላይ የዝናብ ስርጭት የጎርፍ አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል መገለጹን የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል የዜና መጽሔት፤...more16minPlay
August 07, 2025የነሐሴ 1 ቀን 2017 ዓ.ም. የዜና መጽሔትየዜና መፅሔት ጥንቅራችን ኢትዮጵያ ዉስጥ በኤሌክትሪክ ኃይል ላይ የሚደረገዉ ጭማሪ ተገቢ ነዉ መባሉን ከሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ጋር የሚቃኘዉን ዘገባ ያስቀድማል።ሲዳማና ኦሮሚያ ክልልሎች ድንበር ላይ የተደረገዉ ግጭት ሰበብ የግዛት ይገባኛል እንዳልሆነ መነገሩ፣ኦሮሚያ ክልል የአዋሽ ወንዝ ሙላት ሰዉ ማፈናቀሉ፣ ሰሜን ወሎ ደግሞ ለዝናብ ሲፀለይ፣ ዝናብ ተፈናቃዮችን መጉዳቱን የሚቃኙ ዘገቦች በተከታታይ ተስምተዉ ያሳርጋል።...more17minPlay
August 06, 2025የሐምሌ 30 ቀን 2017 ዓ.ም. የዜና መጽሔትበአሮሚያ እና ሲዳማ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በተነሳ ግጭት ሁለት ሰዎች ተገደሉወጣቶች ሞት እንዳለ እያወቁ ለምን በአደገኛ የጉዞ መስመር ይሰደዳሉ? የሕገ-ወጥ ስደት አስከፊ ገጽታ - ከሞት መለስ ያሉ የስቃይ ምዕራፎች ኢትዮጵያዊያንን ለአደገኛ የፍልሰት ጉዞ የሚዳርጓቸው ገፊ ምክንያቶች ምንድናቸው ?...more21minPlay
August 05, 2025የሐምሌ 29 ቀን 2017 የዜና መፅሔትበሕገወጥ መንገድ የሚደረገው ስደት ዛሬም ቀጥሏል፤ በርካቶችም ሕይወታቸውን ማጣታቸው እየተነገረ ነው፤ የወጣት ኢትዮጵያዉያን አደገኛ የባሕር ላይ የስደት ጉዞ ማብቂያዉ የት ነዉ? የሚለው ቀዳሚው የምሽቱ የዜና መጽሔት ዘገባ ነው፤ በትግራይ ክልል ድርቅ የሰዎችን እንስሳትን ሕይወት መቅጠፉ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ለቀጠለው የጦርነት ስጋት የቀረቡ የመፍትሄ ሀሳቦች፤ የቀይ ባሕር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት አስቸኳይ ስብሰባ ፤ እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓመታዊ አፈጻጸም፤ ስኬትና እቅዶቹ የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል የዜና መጽሔት...more22minPlay
August 04, 2025የሐምሌ 28 ቀን 2017 ዓም የዜና መጽሔትየዜና መጽሔት ጥንቅራችን "በግጭት ዐውድ የተባባሰ የሰብዓዊ መብት ጥሰት አለ" አለ ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ማስታወቁ፤ የኦሮሞ ልሂቃን ጥሪ እና የኦነግ መግለጫ ፣ የሰላም ስምምነቶች እስኪፈፅሙ የትግራይ ሠራዊት ወታደራዊ ቁመናውን ጠብቆ እንደሚቆይ መነገሩ፣ ከትግራይ የተፈናቀሉ የአማራ ክልል ተወላጆች ሮሮ ፣እንዲሁም ለምሥራቅ አፍሪቃ ማህበረሰብ አካላት ተደራሽ የሆነ ሁሉን አቀፍ መርሃ ግብር በዋሽንግተን ዲሲ ፤ የተሰኙ ርዕሶችን በስፋት ይዳስሳል...more22minPlay
August 01, 2025የሐምሌ 25 ቀን 2017የዜና መፅሔትየትግራይ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራውን አዲስ ፓርቲ መክሰሱ፤ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዝናብ መታጣቱና የሃይማኖት አባቶች ሕዝቡ ጸሎትና ዱአ እንዲሁም በፍራንክፈርት ጀርመን በመካሄድ ላይ የሚገኘውን በአውሮጳ የኢትዮጵያውያን የስፖርትና ባህል ዝግጅትን የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል የዜና መጽሔት...more15minPlay
July 31, 2025የሐምሌ 24 ቀን 2017 ዓም የዜና መጽሔትየኦሮሚያ ክልል የሥነ-ምግባር ጉድለት አሳይተዋል ያላቸዉን በርካታ ሚሊሻዎች ማባረሩንየትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር የክልሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያሳለፈዉ ዉሳኔ በአዋሽ ሲሽር፣ የኢትዮጵያ የፈዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ደግሞ የሐገሪቱ ምርጫ ቦርድ በሲዳማ ፌደራሊስ ፓርቲ ላይ ያሳለፈዉን ዉሳኔ ሽሯል ፣መሐል አዲስ አበባን ያጥለቀለዉ ጎርፍ ምክንያት የዜና መፅሔት ያስቃኘናል...more18minPlay
July 30, 2025የሐምሌ 23 ቀን 2017 የዜና መፅሔትበሶማሌ ክልል የአስተዳደር መዋቅር፤ የቀጠለው የፓርቲዎች እና ሕዝብ ተቃውሞ፤ የሶማሌ ክልል ምክር ቤት በአዲሱ የወረዳዎች አደረጃጀት ውሳኔ፤ ሂውማን ራይትስ ዎች ሕግ አውጭዎች የሲቪል ድርጅቶች ማሻሻያ ረቂቅ ሕግን ውድቅ እንዲያደርጉ መጠየቁ፤ አብን ለመንግሥትና የፖለቲካ ኃይሎች ያቀረበው የሰላም ጥሪ፤ ናዳ ያስከተለው ስጋት በሺህዎችን ከመኖሪያ አካባቢያቸው ማስለቀቁን የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል የዜና መጽሔት...more21minPlay
FAQs about ዜና መጽሔት:How many episodes does ዜና መጽሔት have?The podcast currently has 1,735 episodes available.