Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ... more
FAQs about ዜና መጽሔት:How many episodes does ዜና መጽሔት have?The podcast currently has 1,993 episodes available.
August 11, 2026የነሐሴ 5 ቀን 2018 የዜና መጽሔትበዜና መጽሔት አራት ዘገባዎችን እናስተነትናለን ። የሕወሓት ታጣቂዎች ላይ የተሰነዘረው የድሮን ጥቃት በአላማጣ፣ ለሰብአዊ መብት ሥጋት የደቀነ «የጦርነት አዝማሚያ» አለ መባሉ፤ በግልገል በለስ ከተማ በደረሰ ጥቃት ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸው እንዲሁም ኢትዮጵያውያን ለሶማሊያ ኅይሎች ያስረከቡት የስምሪት ቀጠና የሚሉ ዘገባዎችን ነው የምናስተነትነው ።...more17minPlay
August 10, 2026የነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔትየዜና መጽሔትኢትዮጵያ እና ኤርትራ - እያደገ የመጣው ውጥረት፤ ከራያ አካባቢ በጦርነት ስጋት የወጣቶችና ሕጻናት በብዛት ለስደት መዳረግ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ድርቅ እና ግጭት ያጠላው ስጋት፤ እንዲሁም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አርሶአደሮች «የእርሻ ማዳበሪያ አልደረሰንም» ማለታቸው መገለጹ፤ የሚመለከቱ ዘገባዎችን አካቷል፤...more19minPlay
August 07, 2026የነሐሴ 1 ቀን የዜና መጽሔትበሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ላይ የሚሳተፉም የማይሳተፉም ፓርቲዎች ስለ ሂደቱ የሰጡት አስተያየት፣አሳሳቢው የሙስና አሻጥር በኢትዮጵያ ፣ "በስውር የአገር ማፍረስ ሴራዎች" ተጠርጥረው ዛሬ ፍ/ቤት የቀረቡ ፖለቲከኞች ለነሐሴ 11 መቀጠራቸው ፣ በጦርነት ትምህርታቸውን ያቋረጡ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ የሚደረግ ጥረት እንዲሁም ጥቂቶችን ተጠቃሚ ያደረገው የድሬዳዋ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ በዜና መጽሔት ዝግጅታችን ትንታኔ የሚቀርብባቸው ርዕሶች ናቸው።...more25minPlay
August 06, 2026የሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔትበዛሬው የዜና መጽሔታችን ስድስት ርዕሰ ጉዳዮችን በትንታኔ እናስደምጣለን ፤ ራያና እና አላማጣ አካባቢዎች ጦርነቱ ማየሉን እና ሴቶች ለቡድን ጾታዊ ጥቃት መዳረጋቸው ፤በሰሜን ኢትዮጵያ ያጠላው የጦርነት ስጋት ፤ ተጎጂዎች እና የአውሮጳ የሰላም ፋውንዴሽን ጥሪ ፤የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ሂደት እና የቀጣይ ሥራዎች ላይ ለዶቼ ቬለ የተሰጠ ምላሽ፤ የዐማራ ግሎባል ፎረም የምክክር ጉባኤውን መቃወሙ፤ ሲፒጄ ለ6 ሃገራት ጋዜጠኞች ሽልማት ሲሰጥ በኢትዮጵያ የታሠሩት እንዲፈቱ መጠየቁ፤ በሳዑዲ አረቢያ የሚመራው የ14 ሀገራት ቅንጅት በይፋ ከተገለጸው አላማ የሰፋ ትርጉም አለው መባሉ፤ በዝርዝር ይደመጣሉ።...more30minPlay
August 05, 2026የሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔትየዜና መጽሔት: ኢትዮጵያና ግብፅ በዓባይ ወንዝ ዉኃ አዘቃቀም ሰበብ የገጠሙት ዉዝግብ ሞቅ ቀዝቀዝ እንዳለ መቀጠሉን የሚቃኘዉን ዘገባ ያስቀድማል። ከወደ ሰሜን ኢትዮጵያ የጦርነት ሥጋት ባንዣበበት ባሁኑ ወቅት የደቡብ ወሎ ወጣቶች፣ የአቅመ-ደካሞችን ቤቶች መጠገንን ጨምሮ ለየአካባቢያቸዉ ሕዝብ 1.4 ቢሊዮን ብር የሚገመት ነፃ አገልግሎት መስጠታቸዉ ተዘግቧል።ለጋምቤላ በተለይ ለኑዌር ዞን የዘንድሮዉ ክረምት የድርቅ ሥጋት አስከትሏል።ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ የወባ በሽታ አለቅጥ ተዛምቷል።ጀርመን ለአፍሪቃ ሕብረት የሰጠችዉ የገንዘብ ድጋፍ የአፍሪቃ ሐገራትን ድንበሮች ለማካለል እየጠቀመ መሆኑ ከአዲስ አበባ ተሰምቷል።...more22minPlay
August 04, 2026የሐምሌ 28 ቀን 2018 የዜና መጽሔትየኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ይስሐቅ ወልዳይ እንዲሁም የፓርቲው አባል ፖለቲከኛ አበበ አካሉ በመንግሥት የፀጥታ ኃይል መታሠራቸውን ፓርቲው ገለፀ።የሰሜን ኢትዮጵያው የጦርነት ስጋት ቀጠናዊ ስጋት ያጭር ይሆን?የሸረሪናው ውጊያ ያሰጋው የከባድ ጦርነት መጀመሪያ ይሆን? "በቀደመው የትግራይ ጦርነት የፍትህና ተጠያቂነት ማጣት ለቀጣይ ግጭት በር ከፍቷል " አምነስቲ...more22minPlay
August 03, 2026የሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔትየዜና መጽሔት ዝግጅታችን ሰሞነኛው የግጭት መረጃ እና የመገናኛ ብዙኃን የይዘት አቀራረብ አንደምታ፤ በትግራይ ድንበር አካባቢ የተቀሰቀሰው ጦርነት በርካቶች ወደ ሱዳን እንዲሰደዱ ማስገደዱ፤ በቆቦ አካባቢ ወታደራዊ ዝግጅት መጠናከሩ እንዲሁም ሕይወት የቀጠፈ የመሬት መንሸራተት አደጋ በጻድቃኔማርያም ገዳም መከሰቱን የሚመለከቱ ዘገባዎችን አካቷል...more19minPlay
July 31, 2026የሐምሌ 24 ቀን 2018 የዜና መጽሔትአንድ የጀርመን ተቋም በኢትዮጵያ ግጭት እንዳይከሰት የሰጠው ምክረ-ሐሳብ፤ ፌደራል ፖሊስ በደቡብ ኢትዮጵያ መስመር በሕገወጥ ሰዎችን የሚያሸጋግሩትን መቆጣጠሩን መግለጹ፤ የተማሩ ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን ኢላማ ያደረገው የኢንተርኔት ማጭበርበር፤ ዋግህምራ ዞን አበርገሌ እና ጻግብጂን የተቆጣጠረዉ ታጣቂ ቡድን ተዋጊዎችን እየመለመለ ነው መባሉ፣ መተከል ዞን ከጉባ-ግልገል በለስ የተበላሸው መንገድ፤ እንዲሄም ሮም ጣሊያን ላይ እየተካሄደ የሚገኘው በአውሮጳ የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል ድግስን የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል።...more28minPlay
July 30, 2026የሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ/ም የዜና መጽሔት1, የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የመረጃ ተደራሽነት ላይ የተሰጡ አስተያየቶች 2, የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤና የሌሎች ሀገሮች ተሞክሮ 3, በትግራይ የተመናመነው ሰብዓዊ ድጋፍ እና የተፈናቃዮች እሮሮ 4, የአዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ በድሬደዋ 5, ጣና ሐይቅን እየፈተነ ያለዉ የእምቦጭ አረም //እንዲሁም6, አፍሪካ ኀብረት በሶማሊያ ያለው ሚና ወደ ፖለቲከዊ ተልዕኮ እንዲሸጋገር መጠየቁ...more27minPlay
July 29, 2026የሐምሌ 22 ቀን 2018 የዜና መጽሔትበዜና መጽኄት አምስት ዘገባዎችን እናስተነትናለን ። ግድያና ጥቃትን የተመለከቱ የምርመራ ውጤቶች ትኩረት አግኝተዋልን? ሲል የሚጠይቀው ቀዳሚው ዘገባችን ነው ። ከ90 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች በ4 ጣቢያዎች ለብርቱ ዝናምና ጎርፍ ተጋልጠዋል መባሉ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዓመቱ ስኬቶች እና ያጋጠሙት ፈተናዎች፤ IOM ምስራቅ አፍሪቃውያን በዓለም አቀፍ ወንጀል እንዲሳተፉ እየተገደዱ ነው ማለቱ እንዲሁም የሰው ሠራሽ አደጋ በማጃንግ ዞን ጥብቅ ደን ላይ አደጋ ደቅኗል ይሰኛሉ ዘገባዎቹ...more21minPlay
FAQs about ዜና መጽሔት:How many episodes does ዜና መጽሔት have?The podcast currently has 1,993 episodes available.