Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ... more
FAQs about ዜና መጽሔት:How many episodes does ዜና መጽሔት have?The podcast currently has 1,993 episodes available.
June 30, 2026የሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔትየዜና መጽሔት ዝግጅታችን የኤርትራ የወደፊት ኅልዉና የፕሬዝደንቷ አገዛዝ ያልነዉን ርዕሥ ያስቀድማል። ዜና መፅሔቱ አዲስ አበባ ዉስጥ በተዘዋዋሪ አዉቶብሶች የዲጅታል የሕዝብ አገልግሎት መሰጠቱ፣ የደቡብ አፍሪቃ መጤ ጠል ቡድናት በከፈቱት ዘመቻ ላይ ሊነጋገር የነበረዉ የአፍሪቃ ሕብረት ስብሰባ መራዘምና የዓለም እግር ኳስ ዋንጫን የሚቃኙ ዘገቦችና ቃለ ምልልስን አካቷል።...more20minPlay
June 29, 2026DW Amharic የሰኔ 22 ቀን 2018 ዜና መጽሔትየሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድ የኢትዮጵያ ጉብኝት፣ በትግራይ የወጣቶች አፈሳ ቀጥሏል መባሉና የአውሮፓ ህብረት ማስጠንቀቂያ፣ የቀነ ገደቡ መጠናቀቅ እና የፍልሰተኞች ሥጋት በደቡብ አፍሪካ...more20minPlay
June 26, 2026የዓርብ ሰኔ 19 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔትዜናዉን የሚለጥቀዉ የዜና መፅሔት ዝግጅታችን ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አዲስ የደነገገዉን ሕግ እንዲሽር ሑማን ራይትስ ዋች ያቀረበዉን ጥያቄ ህወሃት ዉድማድረጉን የሚተነትነዉን ዘገባ ያስቀድማል።ዜና መፅሔቱ፣ የጋቤላ ብልፅግና ፓርቲ ፅሕፈት ቤት ከተቃዋሚዎች ጋር ተባብሮ ለመሥራት ቃል መግባቱ፣ ደቡብ አፍሪቃ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ጥቃት ይደርስብናል የሚለዉ ሥጋታቸዉ መናሩ፣ የመረጃ ጥቅም፣ የአፍሪቃ አቅምና ዝግጅት፣ እንዲሁም የዓለም የእግር ኳስ የዋንጫ ግጥሚያን የሚቃኙ ዘገቦችና አጭር ዉይይቶች አሉት።...more26minPlay
June 25, 2026የሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔትየኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ለምክክር ጉባኤ የመረጣቸው ስምንቱ አጀንዳዎች፤ በአስተያየት ሰጪዎች ተስፋ እና ሥጋት የተንጸባረቀበት አገራዊ ምክክር፤ የኦሮሚያ ክልሉ ግጭት እና ዘላቂ መፍትሄው፤ የኢቦላ ስርጭትን ለመከላከል የጉዞ እገዳ አስፈላጊ አይደለም ሲል ዐአፍሪካ ሲዲሲ ዐሳወቀ፤ በስፔን ከ200 በላይ ሰዎችን የገደለው የሙቀት ወጀብ በፈረንሣይስ ምን አደረሰ?...more25minPlay
June 24, 2026የሰኔ 17 ቀን 2018 የዜና መፅሔትበዛሬው የዜና መፅሔታችን 4 ርዕሰጉዳዮች ይደመጣሉ።በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምሥራቅ ጉራጌ ዞን ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ሦስት የፀጥታ አባላት መገደላቸውን፤የትግራይ ጊዚያዊ መስተዳደር ያረቀቀው አስገዳጅ ወታደራዊ ምልመልን እንዲሰርዝ ሂዩማን ራይትስ ዎች መጠየቁንከተመራጬ መንግስት ምን ይጠበቃል? በሚል መራጮች የሰጡት አስተያየት እንዲሁም የ12 ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን የሚመለከቱ ናቸው በዚሁ ቅደም ተከተል ይደመጣሉ።...more18minPlay
June 23, 2026የሰኔ 16 ቀን 2018 የዜና መጽሔትየዜና መፅሔት ዝግጅታችን ኢትዮጵያ ዉስጥ የተደረገዉን ምርጫ ዉጤት በተመለከተ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሰጡት፣ ድጋፍ፣ ተቃዉሞና ምክርን በሁለት ዘገቦች እንቃኛለን።ከምርጫ ጋር የተያያዘ ነዉ በተባለ ጥራሬ አንድ የቀድሞ ዕጩ መታሰራቸዉን የሚያወሳ ዘገባም ሌላዉ ምርጫነክ ዘገባችን ነዉ።ዜና መፅሔቱ የህወሓት ታጣቂዎች አፋር ክልልን ማጥቃት ሰዎች መግደልና ማቁሰላቸዉንና የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የሚሰራጩ የጥላቻ ንግግሮችን መዘዝ የሚቃኝ ዘገባም አለዉ።...more25minPlay
June 22, 2026የሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ/ም የዜና መፅሔትመጽሄተ ዜናችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ትናንት እሁድ ይፋ ባደረገው 7ኛ ው ጠቅላላ ሃገራዊ የምርጫ ዉጤት ላይ ያተኩራል። በቅርቡ ከኢትዮጵያ የተባረረችው ፈረሳያዊቷ ጋዜጠኛን አስመልክቶ ቀጣሪዋ ላክሮዋ ጋዜጣ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ያቀረበው ወቀሳም በዝርዝር ከሚደመጡ ዘገባዎቻችን አንዱ ነው።...more18minPlay
June 20, 2026የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተጨማሪ ውጤቶችን ይፋ አደረገምርጫ ቦርድ ትናንት ዓርብ ማምሻውን በሰጠው መግለጫ ተጨማሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የክልል ምክር ቤቶች እጩ አሸናፊዎችን ይፋ አድርጓል፡፡ቦርዱ ይፋ ካደረጋቸው ውጤቶች መካከል የአብን ሊቀመንበር ዶ/ር በለጠ ሞላ እንዲሁም የቀድሞ የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ቀጄላ መርዳሳ በግላቸው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወንበር አሸንፈዋል።...more4minPlay
June 19, 2026DW Amharic የሰኔ 12 ቀን 2018 የዜና መጽሔትበሰኔ 12 ቀን 2018 የዜና መጽሔት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ “አክራሪ” ባሏቸው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አባላትና በቤተሰቦቻቸው ላይ የጣሉትን የቪዛ ገደብ የተመለከቱ ሁለት ዘገባዎች ተካተዋል። የውክልና መቀመጫ ያገኙ ፓርቲዎች ቀጣይ መንገድ፣ ሥመ-ጥሩው የሙዚቃ ባለሙያ አዲስ ገሠሠ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፣ ኢትዮጵያ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ሰበብ ከአሜሪካ የሚመጣውን ጫና እንዴት ልትይዝ ይገባል? የሚሉ ዘገባዎችም ይቀርባሉ።...more24minPlay
June 18, 2026የሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔትየዜና መጽሔት ዝግጅታችን ኢትዮጵያን ወደ ባሕር በር መመለስ በአፍሪካ ቀንድ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና የደህንነት ትብብርን ያጠናክራል መባሉ፤ የተቃዋሚ ፓርቲ እጩዎች ቁጥር ሻል ብሎ የታየበት የምርጫ ውጤት፤ መሶብ» የሚል መጠሪያ የተሰጠው የአንድ ማዕከል አገልግሎት፤ በጥብቅ የመንግሥት ቁጥጥር የሚመራው የቤት ኪራይና ዳራው፤ እንዲሁም የክረምት ወራት የአየር ጠባይ ሁኔታ ትንበያን የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል።...more26minPlay
FAQs about ዜና መጽሔት:How many episodes does ዜና መጽሔት have?The podcast currently has 1,993 episodes available.