የዓለም ዜና

DW Amharic የሚያዝያ 05 ቀን 2016 የዓለም ዜና


Listen Later

ኢትዮጵያ በሶማሌላንድ የባሕር ኃይል እንድታቋቁም እንደማትፈቅድ ሶማሊያ አስታወቀች። በውይይት ኢትዮጵያ ለንግድ አገልግሎት ወደብ የምታገኝበትን ዕድል ሶማሊያ ልታጤን እንደምትችል የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናግረዋል። የአፍሪካ ኅብረት ማሊ ወደ ሲቪል አስተዳደር የምትመለስበትን ፍኖተ-ካርታ እንድታቀርብ ጠየቀ። ናይጄሪያ አዲስ የማጅራት ገትር መከላከያ ክትባት ለዜጎቿ መስጠት ጀመረች። ጀርመን የሩሲያን ጥቃት ለመመከት ለዩክሬን ተጨማሪ ፓትሪዮት የአየር መከላከያ ሥርዓት ልትሰጥ ነው። የኢራን አብዮታዊ ዘብ አባላት ከእስራኤል ግንኙነት አለው የተባለ መርከብ ተቆጣጠሩ። በአውስትራሊያ በስለት በተፈጸመ ጥቃት ስድስት ሰዎች ተገደሉ።
...more
View all episodesView all episodes
Download on the App Store

የዓለም ዜናBy DW