የዓለም ዜና

DW Amharic የሚያዝያ 20 ቀን 2016 የዓለም ዜና


Listen Later

በኬንያ ከመጋቢት ጀምሮ እየጣለ የሚገኘው ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 76 አሻቀበ። ሱዳን በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች “ትንኮሳ” ላይ የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት በአስቸኳይ እንዲወያይ ጥያቄ አቀረበች። የፖርቹጋል መንግሥት አፍሪካውያን በባርነት ሲሸጡም ሆነ በቅኝ ግዛት ወቅት ለተፈጸሙ ወንጀሎች ካሳ ለመክፈል ምንም አይነት ሒደት እንደማይጀምር አስታወቀ። ወግ አጥባቂው የእስራኤል የፋይናንስ ሚኒስትር ቤዛሌል ስሞትሪች በራፋ የታቀደው ወረራ ከተሰረዘ የጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁን መንግሥት እንደሚያፈርሱ ዛቱ። ሁለት ዩክሬናውያን በላይኛው ባቫሪያ በስለት ተወግተው መገደላቸውን የጀርመን ፖሊስ አስታወቀ።
...more
View all episodesView all episodes
Download on the App Store

የዓለም ዜናBy DW