የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን አቶ ኤርሚያስ አመልጋን ጨምሮ “በሕገ-ወጥ መንገድ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ለሕዝብ ሽያጭ በማቅረብ ገንዘብ ሲያሰባስቡ ነበር” ተብለው በተጠረጠሩ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ላይ ምርመራ ጀመረ። የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ቻይና ሠራሽ የጦር መሣሪያዎች ለሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ማቅረቧን እንዳረጋገጠ አምስነቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ። የጀርመን ፕሬዝደንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር በዩክሬን ጦርነት የምትነዛውን ታሪካዊ ውሸት ነቀፉ። ሩሲያ የድል ቀንን ለመዘከር ስትዘጋጅ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን እና የቻይና አቻቸው ሺ ጂን ፒንግ ለምዕራቡ ያላቸውን እምቢተኝነት በግልጽ አሳይተዋል።