የዓለም ዜና

DW Amharic የነሐሴ 13 ቀን 2016 የዓለም ዜና


Listen Later

በምርጫ ቦርድ እውቅና የተነፈገው የህወሓት 14ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ደብረፅዮን ገብረሚካኤልን ሊቀ-መንበር አድርጎ መረጠ። አቶ አማኑኤል አሰፋ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳን በመተካት ምክትል ሊቀ-መንበር ሆነው ተመርጠዋል። የኬንያ መንግሥት ተቃውሞ በቀሰቀሰው የፋይናንስ ደምብ ውስጥ ተካተው ከነበሩ ቀረጦች የተወሰኑትን ሥራ ላይ በማዋል 1.2 ቢሊዮን ዶላር የመሰብሰብ ዕቅድ እንዳለው የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣን አስታወቁ። የተባበሩት መንግሥታት ተቀባይነት ከሌለው ደረጃ ደርሷል ያለውን የርዳታ ሠራተኞች ግድያ አወገዘ። ብዙ የርዳታ ሠራተኞች ከተገደሉባቸው አስር ሀገራት አንዷ ኢትዮጵያ ናት።
...more
View all episodesView all episodes
Download on the App Store

የዓለም ዜናBy DW