የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ወደ ምትገኘው ነቀምቴ በሣምንት ሦስት ቀናት በረራ መጀመሩን አስታወቀ። የእስራኤል ጦር በደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ የሰብአዊ ርዳታ አቅርቦትን ለማሳደግ በየዕለቱ ለሰዓታት ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንደሚገታ አስታወቀ። በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል እየተካሔደ የሚገኘውን ጦርነት ለማብቃት ያለመ ማንኛውም የሰላም ሥምምነት መሠረት የዩክሬን የግዛት አንድነት ሊሆን እንደሚገባ ሰማኒያ ሀገሮች ጥሪ አቀረቡ። በአውሮፓ ዋንጫ የምድብ አራት የመጀመሪያ ጨዋታ ኔዘርላንድስ ፖላንድን 2 ለ 1 አሸነፈች።