አርዕስተ ዜና
-የዩኤስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር፤ ከቻይና በሚገቡ ምርቶች ላይ የተጣለውን 10 በመቶ ታሪፍ ተከትሎ፤ ቻይና የአጸፋ እርምጃ እንደምትወስድ አስታወቀች።
-የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ኬንያ ያቀረበችበትን ክስ አስተባበለ። ድርጅቱ ማስተባበያ የሰጠዉ፤ የኬንያ ፖሊስ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን በሕገ ወጥ የጦር መሣሪያና አደዛዥ እጽ ዝውወር ብሎም በሰዎች እገታ ክስ መግለጫ ማዉጣቱን ተከትሎ ነዉ።
-በጎጂ ዞን ሳባ ቦሩ ወረዳ በባህላዊ መንገድ ማዕድን እያወጡ በነበረው ሰዎች ላይ በደረሰው የመሬት መደርመስ የስምንት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰማ።