በምሥራቃዊ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሚንቀሳቀሱ ሁሉም ታጣቂ ቡድኖች ግጭት እንዲያቆሙ የኬንያ ፕሬዝደንት ጥሪ አቀረቡ። የሱዳን ጦር በኻርቱም ባሕሪ የተባለ አካባቢ መቆጣጠሩን አስታወቀ። በማሊ በሀገሪቱ ጦር እና የሩሲያው ቫግነር ቅጥረኛ ወታደሮች አጀብ የሚጓዝ የተሽከርካሪዎች ቅፍለት ላይ በተፈጸመ ጥቃት 32 ሰዎች ተገደሉ። ሐማስ ሦስት ታጋቾችን፤ እስራኤል 183 ፍልስጤማውያንን በቀይ መስቀል በኩል ተለዋወጡ። ዩክሬን በሩሲያ ኩርስክ ግዛት ጥቃት መጀመሯን ፕሬዝደንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ አረጋገጡ። ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ቱሩዶ ዶናልድ ትራምፕ ካናዳን ወደ አሜሪካ ለመጠቅለል ያቀረቡት ሐሳብ ተጨባጭ እንደሆነ አስጠነቀቁ።