መቀመጫውን በኒው ዮርክ ያደረገው ፊች ሬቲንግስ ኢትዮጵያ 33 ሚሊዮን ዶላር ወለድ ሳትከፍል መቅረቷ ከተረጋገጠ በኋላ በዓለም ገበያ የተሸጠውን ቦንድ ምድባ ወደ ያልተከፈለ ዝቅ አድርጎታል። መንግሥት እና የኢትዮጵያ ቦንድ ባለቤቶች በወለድ እና ዕዳ አከፋፈል ላይ እየተደራደሩ ነው። የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ሁሉም አበዳሪዎች እኩል መስተናገድ አለባቸው በሚል አቋማቸው እንደጸኑ ነው። ኢትዮጵያ ከግል አበዳሪዎች ቦንድ ሸጣ የተበደረችው አንድ ቢሊዮን ዶላር ከአጠቃላይ የውጭ ዕዳ ያለው ድርሻ ሁለት በመቶ ገደማ ነው።