ጌታችን በምድር በተመላለስበት ጊዜ አባቱን በሙላት አስደስቶ ነበር። ያስደሰተበትም መንገድ በምልልሱ ነበር — ይኸውም በመንፈስ እንጂ በስጋ ሃሳብ ባለመመላለስ። ጌታም በተደጋጋሚ የኣባቱን ፍቃድ እንጂ የራሱን ፈቃድ ሊያደርግ እንዳልመጣ የተነገረውን መልዕክት ቅዱሳን መጽሐፍት በተለያየ ሥፍራ ዘግበዎል። አባቱን በሙሉ በማስደስት እግዚአብሔር ለማስደስት የሚያስችለውን ፈለግም ትቶልናል። አብ ደስ በተስኘ ቁጥር፤ ደስ ላስኙት ዋጋን ውይም ብድራትን ይከፍላቸው ነበር። […]