Great Truths Podcast (Amharic)

Great Truths Podcast (Amharic)

By ዶ/ር ቤንጃሚን ዲንArts
Download on the App Store

Great Truths Podcast (Amharic) episodes

  • መላእክት #6 | መላእክት በምድር ላይ ዋናው ተግባራቸው ምን ይመስላል?

    በምድር ላይ የመላእክት ዋናው ሥራቸው ወይም ተግባራቸው እግዚአብሄርን ማምለክና ማገልገል ነው፡፡ በሰማይ ያላቸው የተለምዶ ሥራቸውም እግዚአብሄርን ማመስገን ሲሆን በተለየና ባልተለመደ ሁኔታ ደግሞ ስናየው የእግዚአበሄርን ታሪካዊ የመዋጀትና የመታደግ ሥራውን ወደ ህዝቡ ዘንድ ማሳለጥ ነው፡፡ በመጽሃፍ ቅዱሳችን ውስጥ ገና ከመጀመሪያው አካባቢ ጀምሮ የጌታ መላኣክ ወይም የእግዚአብሄር መልኣክ የሚሉ ሃሳቦች ከእግዚአብሄር ከራሱ ሥራና ተግባር ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡

    21 min
  • መላእክት #5 | መላእክት በምን ዓይነት መልክ ይገለጣሉ ወይም ይታያሉ?

    በተለምዶ መላእክት ለሰው ልጆች በሥጋ ዓይን የሚታዩ ፍጥረታት አይደሉም፡፡ በመጽሃፍ ቅዱሳችን ውስጥ መላእክት በወንዶች መልክ የሚገለጡ ፍጥረታት ናቸው (ዘፍ. 18፡2፤ቁ. 16፤፤ 19፡1-22 መሳፍ. 13፡3-21፤ እብ 13፡2)፡፡ ከመለኮታዊ ሥልጣናቸው የተነሳ አንዳንዴ መላእክት የሚያስፈሩ ናቸው፡፡ በተፈጥሮ ባህሪያቸው መላእክት በሚታይ መልኩ ሲገለጡ የሚያስፈራ ሳይሆን በልዩ የእግዚአብሄር ክብርና ግርማ የተሞሉ እና በሚያስደንቅ ሁኔታም የሚገለጡ ናቸው (ዘኁ. 22፡31፤ 2 ነገስት 6፡17፤ ዳን. 10፡4-9፤ ማቴ. 28፡3፤ ሉቃ. 2፡9 እና ራእይ 10፡1-3)፡፡ በጥቂቱ ሊያስደንቀን የሚሞክረው ነገር ቢኖር ዮሃንስ ሁለት ጊዜ የእግዚአብሄርን መልእክት ወደርሱ ያመጣውን መልኣክ ሊያመልከው ወይም ሊሰግድለት ሞክሮ ነበር፡፡ ነገር ግን መልኣኩ ራሱ ይህንን ጉዳይ እንደተቃወመው እንመለከታለን (ራእይ 19፡10 እና 22፡8)[1]፡፡ ይህም ማለት መላእክት ለእግዚብአሄር የሚገባውን ክብር ለራሳቸው ለማድረግ እንደማይፈልጉ ነው፡፡

    17 min
  • መላእክት #4 | በአጠቃላይ የአቋማቸው ሁናቴ ምን ይመስላል?

    መጽሃፍ ቅዱሳችን በግልጽ እና ያለምንም ማመንታት እንደሚነግረን መላእክት ከእግዚአብሄር በታች የሆኑ ፍጥረታትና በእርሱ እቅድና ፈቃድ ብቻ የሚመላለሱና የሚመሩ ናቸው፡፡ ስለዚህ በመላእክትና በእግዚእበሄር መሃል ያለው ልዩነት ግልጽ ነው፡ ምክኒያቱም እነርሱ የእርሱ ናቸውና (መዝ. 104-4)፡፡ እያንዳንዳቸውም በየግላቸውና በተለየ ሁኔታ በእግዚአብሄር በራሱ፤ ለእርሱም ክብር ለሚሆን አገልግሎት የተመረጡ ናቸውና (1 ጢሞ. 5፡21)፡፡ እንዲሁም እንደ እግዚአብሄር ያለ ማን ነው; የሚል ትርጉም ያለው የሚካኤል እና እግዚአብሄር ኃያል ነው የሚል ትርጉም ያለው የገብርኤል የስሞቻቸው ትርጉም በመላእክቱና በእግዚአብሄር መሃል ያለውን በምንም ዓይነት ሁኔታ የማይቆረጠውን ግንኙነት ያሳያል፡፡

    3 min
  • መላእክት #3 | በሰማያዊ ሥፍራ መደራጀታቸውና ልዩ ሚናቸው

    መላእክት የሚኖሩት በሰማይ ነው (ሉቃስ 2፡15)፡፡ በሰማያዊው ዙፋኑም ፊት ለፊት እግዚአብሄር የሚያዛቸውን ሁሉ ይታዘዙታል፡፡ ለእግዚአብሄር አገልግሎትና ፈቃዱንም ለማድረግ እንዲሁም እርሱን ለማመስገንና ለማምለክ ሁልጊዜ የተዘጋጁ ናቸው (መዝ. 103፡2021)፡፡ የእግዚአብሄርንም ፊት እያዩ ያመልኩታል (ማቴ 18፡10)፡፡ በአጭሩ ሲገለጽ የመላእክት ሥራቸው በሰማያት ሆነው እግዚአብሄርን መታዘዝ፤ ማምለክና ማመስገን ነው፡፡

    18 min
  • መላእክት #2 | የተፈጥሮ ችሎታና አቅም

    መልኣክ የሚለው ቃል መጽሃፍ ቅዱስ በተጻፈባቸው በሁለቱ ቋንቋዎች የሚለውን ለመረዳት መሞከር ይጠቅመናል፡፡ በእብራይስጥ ቋንቋ (mal’ak) ማልኣክ የሚል ሲሆን በግሪክ ቋንቋ ደግሞ (angelos) አንጅሎስ ይላል፡፡ ይህም የሚያመለክተን የመላእክት ዋናው አገልግሎታቸው እና ተግባራቸው  ዜና ተሸካሚዎች እና አስተላላፊዎች፤ አዋጅ ነጋሪዎችና መልእክተኞች  እንደሆነ ነው፡፡

    16 min
  • መላእክት #1 | መንፈሳዊው ዓለምና የመላእክት መገኛ ሥፍራ

    በመጽሃፍ ቅዱሳችን የመጀመሪያው ዐረፍተ ነገር በመጀመሪያ እግዚአብሄር ሰማይንና ምድርን እንደ ፈጠረ ይነግረናል። ይህም የሚያሳየን እኛ የምንኖርበት ዓለም ሁለት ዓይነት እንደሆነ እና የእግዚአብሄር ዓለም በሁለት ክፍል የተከፈለ እንደሆነ ነው፡፡ እኛ የሰው ልጆች ሁላችን ማንም ሊያየንና ሊረዳን በሚችልበት ሁኔታ የተፈጠርን በቁሳዊ ዓለም የምንገኝ ፍጥረታት ስንሆን መላእክት ግን ሙሉ በሙሉ ከኛ በላይ ሆነው በሰማያዊ ሥፍራዎች የሚገኙ መንፈሳዊ ፍጥረታት ናቸው፡፡ ስለዚህ ስለ መላእክት ትክክለኛውን ግንዛቤ ሊሰጠን የሚችለው እግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡ ይህንንም እግዚአብሄር የሚያደርገው በሰማይና በምድር ባለው በጌትነቱ ሥልጣን የቃሉን (የመጽሃፍ ቅዱስን) እውነት በመጠቀም ነው፡፡ መጽሃፍ ቅዱስ ብቸኛው የዚህ እውቀት ምንጩ ሊሆን ይገባል፡፡

    17 min
  • የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል#6 | በወንጌል ያለ አንድነት

    በዘር፤ በጾታ፤ በማህበራዊ፤ በኢኮኖሚያዊና በፖለቲካዊ ጉዳዮቻችን ከመለያየታችን ባለፈ እኛ ክርስቲኖች ሁላችንም በፍቅርና በአንድነት እንድንኖረና ለሌሎችም መልካም ምሳሌዎች እንድንሆን ታዘናል (የዮሃንስ ወንጌል 13፡34-3፤ ገላቲያ 3፡28-29)፡፡ እንዲሁም ደግሞ በተቻለ መጠን ሁሉ በአእምሮኣችን አስተሳሰብና በመሳሰሉት ነገሮቻችን ሁሉ አንድ እንድንሆን ተጠርተናል (ዮሃንስ 17፡20-21፤ ፊልጵስዩስ 2፡2፤ ሮሜ 14፡1-15፡13)፡፡ በክርስቲኖች መሃል ክፍፍል ሲፈጠር ለዓለም የምንመሰክረውን ምስክርነታችንን እንደደሚያደናቅፍብን ልናውቅ ገባናል፡፡ በክርስቲናዊ አስተምህሮችም መሃል በተለያዩ ዓይነት ክርክሮች አማካኝነት የሃሳብ ልዩነቶች ሲፈጠሩ የጋራ እምነቶቻችን እተሸረሸሩና  ልዩነቶቻችን እየሰፉ ሲሄዱ የህይወታችን ዋናው ዓላማ የሆነው አንድነታችን እየተዳከመ በመሄድ ለሁለተኛና ለሦሥተኛ ጉዳዮቻችን ሥፍራችንን እየለቀቅን እንሄዳለን ማለት ነው፡፡

    22 min
  • የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል#5 | የወንጌል ምንነት ማጠቃለያ

    በመጽሃፍ ቅዱሳችን ውስጥ “ወንጌል” የሚለው ቃል ለየት ያለ ቃል ነው፡፡ ቃሉ አጭርና ውስን ቢመስልም በብዙ መንገዶች ሊገለጹ የሚችሉ ልዩ ልዩ ሃሳቦችንና መልእክቶችን የያዘ ቃል ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል፡- በመጀመሪያ ደረጃ በብሉይ ኪዳን ዋና እምብርት ላይ የተጠቀሱትን የድነትን ተስፋዎች ሁሉ አቅፎ በመያዝ ጉዳዩን በሚገባ ያብራራል፡፡ ቀጥሎ ደግሞ የናዝሬቱ ኢየሱስ በስሙ ለሚያምኑ ሁሉ ያዘጋጀውን መልካም ዜና ግልጽ አድርጎ ይነግረናል፡፡ እንዲሁም  ሰዎች ስለ ክርስቶስ የተነገረውን እውነት እና የእግዚአብሄርን የማዳን ሥራውን በሚገባ እንዲረዱ ለአድማጮች ሁሉ ግልጽ ያደርገዋል፡፡ በመጨረሻም፡- ይህ “ወንጌል” የሚለው ስም ራሱ በቀደመቺው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ልዩ ሥፍራ ተሰጥቶት የኢየሱስን ታሪክና ድንቅ ሥራዎቹን መናገር ብቻ ሳይሆን ለሚቀጥለውም ትውልድ ሊተላለፍ በሚችልበት ሁኔታ በአዲስ ኪዳናችን ውስጥ ተጽፎ ይገኛል፡፡ ስለዚህ በመጽሃፍ ቅዱሳችን ውስጥ “ወንጌል” የሚለው ቃል በተለየ ሁኔታና መልክ የምንረዳው ቃል ቢሆንም ለሁሉም ሰው ሊሆን በሚችል መልኩ በቀላሉ ሊገለጽ የሚችል የእግዚአብሄር መልእክት ነው፡፡ 

    24 min
  • የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል#4 | አምስት ማጣፈጫዎች ክፍል 3

  • የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል#3 | አምስት ማጣፈጫዎች ክፍል 2

About Great Truths Podcast (Amharic)

From the publisher's feed

This is the Amharic version of the Great Truths Podcast.

ይህ ፖድካስት የእግዚአብሔር ቃልን በተሻለ መንገድ ለመረዳት እና የመፅሐፍ ቅዱስን መልዕክት ዛሬ ለእኛ ምን እንደሆነ ለማወቅ ይረዳናል። ታላቅ እውነት (Great Truths) ለትርፍ ያልተቋቋመ፣ ከ 10 ሚሊዮን…