እግዚአብሔር የችግሮች ሁሉ መፍትሔ ነው። የእርሱን መገኘት ስንይዝ፤ የእርሱ ጥበብ እና ኃይልም ሲሞላን እኛን እግዚአብሔር ካየልን ነገር ለማስቆም የሚበረታ እንቅፋት እንደሌለ ልናውቅ ይገባል። ይህን ነው በእግዚአብሔር ፈጽሞ መደገፍ የምንለው። በየለቱ በመግባት በመውጣታችን ከጭንቀት ነጻ የሆነ እና በመተማመን የተሞላ ሕይወትን ለመኖር የእግዚአብሔር ቃል እንደ ሁለንተናችን ሆኖ እንዲዏሃደን ልናደርግ ይገባል። እንደዚህ ስናደርግ ቃሉ እግዚአብሔር ያለንን እንድናገኝ እና […]