ክፍል 11፡ የለውጥ መድረኮች: የትያትር ኃይል ለዘላቂ ለውጥ እንግዳ፡ መዓዛ ወርቁ፤ ጸሐፊ ተውኔት አቅራቢ፡ ተሾመ ወንድሙ በዚህ የኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ ኢትዮጵያ ፖድካስት ከዝነኛዋ ጸሐፊ ተውኔት መዓዛ ወርቁ ጋር በመሆን በኢትዮጵያ የባህል ተረክ ውስጥ ትያትር የተጫወተውንና እየተጫወተ ያለውን ከፍተኛ ሚና እንዳስሳለን፡፡ በትምህርት ቤቶች እና ሆቴሎች ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ፤ሀገርን ለአንድ ዓላማ እስከማስተባበር ድረስ፣መዓዛ የኢትዮጵያ ትያትር አስደማሚ ጉዞን ታስቃኘናለች፡፡ በተጨማሪም ትያትር ለፊልም፣ቴሌቪዥን፣ትምህርት፣የሀገር ግንባታ ያለውን አስተዋጽኦ እንዲሁም የጋራ ማንነትን በመቅረጽ ረገድ ያለውን አስተዋጽኦ ጸሐፊ ወደ ኋላ በመመለስ ትዳስሳለች፡፡ በዚህ ክፍል የሚከተሉትን እናነሳለን • የኢትዮጵያ ትያትር ጥልቅ ታሪክ • ትያትር በኢትዮጵያ ፊልም እና ቴሌቪዥን ላይ የሚሳተፉ ባለተሰጥኦዎችን እንዴት ኮትኩቶ እንዳሳደገ • ኪነ-ጥበብ ለህብረተሰብ እድገት እና ውይይት ለምን አስፈላጊ እንደሆነ • የፖሊሲ፣የገንዘብ ድጋፍ እና ውይይት ከፍተኛ አስፈላጊነት • የትያትር መጻኢ እጣ ፈንታ በኢትዮጵያ እና አፍሪካ ይህ ለአርቲስቶች፣ፖሊሲ አውጪዎች፣ተማሪዎች እንዲሁም በባህል የለውጥ ኃይል ለሚያምኑ ሁሉ ጥልቀት ያለው ምልከታን የሚሰጥ እንዲሁም ወቅታዊ ውይይት ነው፡፡ በኢትዮጵያ የፈጠራ እና የባህላዊ ኢንዱስትሪ ላይ ተጨማሪ ውይይቶችን ለመከታተል ሰብስክራይብ ያድርጉን እንዲሁም አዲስ ክፍሎች እንዳያመልጥዎት የደወል ምልክቱን ይጫኑ! Episode 11: "Stages of Change: The Transformative Power of Theatre" Guest: Meaza Worku (Playwright) Host: Teshome Wondimu In this episode of the Connect for Culture Africa – Ethiopia Podcast, we sit down with acclaimed playwright Meaza Worku to explore the powerful role theatre has played—and continues to play—in Ethiopia's cultural narrative. From its early beginnings in schools and hotels to its role in national mobilization, Meaza takes us through the remarkable journey of Ethiopian theatre. She reflects on its contribution to film, TV, education, nation-building, and the shaping of collective identity. We discuss: • The deep-rooted history of Ethiopian theatre • How theatre cultivated Ethiopia's film and TV talent • Why art is essential for societal growth and dialogue • The crucial need for policy, funding, and private-sector support • The future of theatre in Ethiopia and Africa This is an insightful and timely conversation for artists, policymakers, students, and anyone who believes in the transformative power of culture. Subscribe for more conversations on Ethiopia's creative and cultural industries. Don't forget to turn on notifications so you don't miss upcoming episodes! #1percentforculture #sustainablepublicfunding #ConnectForCultureAfrica #Theatre #CreativeIndustry