ZereSew ዘረ-ሰው Podcast

ታላላቅ መጻሕፍት — Shakespeare: Hamlet


Listen Later

“To be, or not to be — that is the question.”

ትምህርት 08 | 4 ክፍሎች | አቅራቢ: ሳባ & ኢብሳ & አበባ | ውይይት: ዳዊትና ትግስት

William Shakespeare (1564–1616) — ከ Stratford ትንሽ ከተማ የመጣ፣ ዩኒቨርሲቲ ያልገባ ግን ሰውን ከማንም በላይ ያየ ዓይን። ልጁ Hamnet ሞቶ ለአራት ዓመት ዝም ካለ በኋላ Hamlet ን ፈጠረ — አባቱን ያጣ ልዑል “መኖር ወይስ አለመኖር” ብሎ ጠየቀ። “ወደፊት ሂድ — በቀል ምንም አይቀይርም” — ያ ነው Hamlet ያስተማረው።

ክፍል 1 — Shakespeare ማን ነበር? (ሳባ)

* የ Stratford ልጅ — በ1564 ተወለደ። አባቱ ጓንት ሠሪ — ከክብር ወደ ውርደት ወደቀ — ልጁ ያንን ውድቀት ከቅርብ አየ፣ ኋላ ንጉሦች ሲወድቁ ጻፈ።

* ዩኒቨርሲቲ አልገባም — Grammar School ብቻ — ጥበብ ከዲፕሎማ ሳይሆን ከመመልከት ይወለዳል።

* Anne Hathaway — ገና 18 ዓመቱ ሳለ አገባ — ሦስት ልጆች ወለዱ — Susanna፣ መንትዮች Hamnet እና Judith።

* “የጠፉ ዓመታት” — ከ1587 እስከ 1590 ምንም ሰነድ የለም — ከ Stratford ወጥቶ London ገብቶ ቲያትር ዓለም ውስጥ ታየ።

* ከሞት ጋር መኖር — ቸነፈር London ያጭዳል — ቲያትር ቤቶች ይዘጋሉ — ሕይወትና ሞት ጎን ለጎን ነው።

* Hamnet ሞተ — በ1596 ልጁ ሞተ — 11 ዓመት — ስለ ሐዘኑ አንድ ቃል አልጻፈም። ከአራት ዓመት በኋላ Hamlet ን ጻፈ — ያ ዝምታ Hamlet ሆኖ ወጣ።

* ሰውን ያየበት ዓይን — ያለ ሃይማኖት ስብከት “ሰዎች ለምን ያሉትን ያደርጋሉ?” ብቻ ጠየቀ — ቅናት፣ በቀል፣ ፍቅር፣ ስልጣን — ሁሉንም በቃላት ገለጸ።

ክፍል 2 — Elizabethan England (ኢብሳ)

* ንግሥት Elizabeth — ልጅ ያልወለደች — “ወራሽ ማን ይሆናል?” ያስጨነቀ ጥያቄ — Hamlet ውስጥ ዙፋን ቅሚያ — ተመልካቾቹ ስለ England ያስቡ ነበር።

* ካቶሊክ vs. ፕሮቴስታንት — ስለ ሥልጣን በግልጽ መናገር አይቻልም — ቲያትር ስለ ዴንማርክ ያወራል፣ ተመልካቾቹ ግን ስለ England ያዳምጣሉ — ቲያትር የፖለቲካ ድብቅ ቋንቋ ነው።

* ቲያትር ለሁሉም — Globe Theatre ውስጥ ባላባቶች ከላይ፣ ተራ ሰዎች penny ከፍለው ቆመው — Shakespeare ሁለቱንም ማድረስ ነበረበት።

* ቲያትር ከግንቡ ውጭ — Puritans “የዲያብሎስ ቤት” ይሉት ነበር — Globe Theatre 1613 ተቃጠለ።

* Renaissance — ሰዎች ከመካከለኛው ዘመን ማዕቀፍ ውጭ ማሰብ ጀመሩ — Hamlet ዘመናዊ ሰው ነው፣ ጥያቄ ይጠይቃል ግን ማሰቡ ሲበዛ ድርጊቱ ይዘገያል።

* ለምን ያ ዘመን? — Hamlet አሮጌና አዲስ ዓለም ሲጋጩ ብቻ ሊወለድ ይችላል — መካከለኛ ዘመን “ተበቀል” ይላል፣ Renaissance “ለምን?” ይጠይቃል — Hamlet ያ “ለምን?” ስለ ገባው ሊበቀል ያልቻለው።

ክፍል 3 — ወደ ተውኔቱ (አበባ)

ገጸ ባሕሪያት

* ኀምሌት — የምድረ-ዴን ልዑል፣ አሳቢ፣ ፈላስፋ — ድርጊትን ወደ ኋላ የሚስብ

* ገላውዴዎስ — ወንድሙን ገድሎ ዙፋን የያዘ — ገዳይ ግን ሕሊና ያለው

* ገርትረድ — ኀምሌት እናት — ደካማ ወይ ክፉ? Shakespeare ክፍት ትቶታል

* ወፌ-ይላ (Ophelia) — ኀምሌትን ትወዳለች — ፍቅሯ ዋጋ ያስከፍላታል — ቀልቧ ተሰልቦ ሞተች

* ጶሎኔዎስ — አፈ-ንጉሥ — “ለራስህ ታማኝ ሁን” ያለ ግን ራሱ ሰላይ

* ሆራትዮስ — ብቸኛ እውነተኛ ወዳጅ

* ላርቆስ — ወፌ-ይላ ወንድም — ለበቀል ቸኩሎ Claudius ሰይፍ ሆነ

* ፎርጠንብሮስ — የ Norway ልዑል — ድርጊት ያለው ሰው — ዙፋኑን አገኘ

ታሪኩ — ገቢር በገቢር

ገቢር 1 — ጣዕረ መንፈስ ተናገረ — “ደሜን ተበቀላት — ገዳዩ ወንድሜ ገላውዴዎስ ነው” — ኀምሌት ዕብደት ሊስል ወሰነ።

ገቢር 2 — ኀምሌት ዕብደት ሲያስመስል — ሮዘንቅሮስና ገድለ ስምዖን ሰላዮች ሆኑ — ተዘዋዋሪ ቲያትር ተዋናዮችን አገኝቶ ዕቅድ ዘረጋ — “The Mousetrap” ቲያትር አዘጋጅ።

ገቢር 3 — “To be, or not to be” — ቲያትሩ ሲቀርብ ገላውዴዎስ በርግጎ ወጣ — ማስረጃው ጸደቀ — ግን ቤተ ጸሎት ውስጥ ሊገድለው ሲችል “ሲጸልይ ከገደልኩት ነፍሱ ትዳናለች” ብሎ ቆመ — ከዚያ መጋረጃ ጀርባ ጶሎኔዎስን ሳያውቅ ገደለ።

ገቢር 4 — ኀምሌት ወደ እንግሊዝ ተሰደደ — ማዘዣውን ቀይሮ ሰላዮቹ ፈንታ እንዲገደሉ አደረገ — ተመልሶ ወደ ምድረ-ዴን ገባ — ወፌ-ይላ ቀልቧ ተሰልቦ ሞተች — ላርቆስ ለበቀል ተነሳ — ገላውዴዎስ ሰይፍ በመርዝ እንዲነከር አሳሳበ።

ገቢር 5 — ራስ ቅል — “ዮሪቅ ነበር ይህ — ስልጣን፣ ሀብት፣ ዝና — ሁሉ ወደዚህ ይመጣ” — ፍልሚያ — ገርትረድ መርዝ ጠጥታ ሞተች — ላርቆስ ኀምሌትን በመርዝ ሰይፍ ወጋ — ሰይፍ ተቀያይረው ሁለቱም ተበከሉ — ላርቆስ ሚስጥሩን ተናዘዘ — ኀምሌት ገላውዴዎስን ገደለ — “ቀሪው ዝምታ ነው” — ፎርጠንብሮስ ባዶውን ዙፋን ተቀበለ።

ዋናው ትምህርት

“Move on. Vengeance will change nothing.” — ወደፊት ሂድ፣ በቀል ምንም አይቀይርም።

ክፍል 4 — ውይይት (ዳዊትና ትግስት)

* ፍትሕ vs. በቀል — ፍትሕ ሥርዓት ይፈልጋል፣ በቀል ስሜት ብቻ ነው — Hamlet ማስረጃ ሰብስቦ ፖለቲካ ተጠቅሞ ማጋለጥ ይችል ነበር — ግን ግል በቀል መረጠ።

* ሐዲስ ዓለማየሁ ግንኙነት — “ፍቅር እስከ መቃብር” ተመሳሳይ ጥያቄ — ግለሰብ ራሱ ዳኛ ሲሆን ውጤቱ ጥፋት ነው።

* Gertrude — ክፉ ሳትሆን ደካማ — ልጇን ትወዳለች — መርዝ ያለውን ወይን ስትጠጣ ልጇ እንዳይጠጣ ራሷ ጠጣች ብለው የሚተረጉሙ ሊቃውንት አሉ።

* ማመንታት — Hamlet ያስብ ይቆያል ግን አያደርግም — ጶሎኔዎስን ሲገድል ደግሞ ያለ ማሰብ ወጋ — ሁለቱም ጽንፎች ጥፋት ናቸው — ሚዛን ያስፈልጋል።

* Fortinbras — Hamlet ሲያስብ Fortinbras ይሠራል — Hamlet ሲሞት ዙፋኑን ያገኛል — ያለ ሴራ፣ ያለ በቀል።

* ሐዘንን ይዞ ወደ ፊት — ሐዘን ወደ ፊት ሲሄድ ጥንካሬ ነው፣ ወደ ኋላ ሲሄድ ጥፋት ነው — Hamlet ወደ ኋላ ሄደ።

ያልተነገሩ ነገሮች

* Shakespeare ለሚስቱ “ሁለተኛውን ምርጥ አልጋ” ብሎ ኑዛዜው ውስጥ ትቶላታል — ለምን ሁለተኛውን? ማንም አያውቅም

* Hamlet ከዓለም ሥነ ጽሑፍ ረጅም ሚና ነው — 1,475 ገደማ ስንኞች — ከ4 ሰዓት በላይ መድረክ ላይ

* Globe Theatre 1613 “Henry the Eighth” ሲቀርብ ተቃጠለ — ሦስት ሺ ሰዎች ነበሩ — አንድ ሰው ብቻ ተጎዳ — ሱሪው ላይ እሳት ቢራ አጠፉት

* ጀርመንኛ ትርጉሙ (August Wilhelm Schlegel) ከ Shakespeare ጋር ተወዳዳሪ ነው ይባላል — ጀርመኖች “የእኛ Shakespeare” ይሉታል

* Kronborg Castle (Elsinore) ዛሬም አለ — በየዓመቱ Hamlet ይቀርብበታል — Shakespeare ራሱ ዴንማርክ ሄዶ አያውቅም

ቁልፍ ጥቅሶች

“To be, or not to be — that is the question.” — ኀምሌት

“The rest is silence.” — “ቀሪው ዝምታ ነው።” — ኀምሌት

“To thine own self be true.” — “ለራስህ ታማኝ ሁን።” — ጶሎኔዎስ

“ዮሪቅ ነበር ይህ — ስልጣን፣ ሀብት፣ ዝና — ሁሉ ወደዚህ ይመጣ።” — ኀምሌት

“Move on. Vengeance will change nothing.” — ፕሮፌሰሩ

“Mediocre minds invariably hate genius.” — ፕሮፌሰሩ

ስሞችና ቃላት

ሰዎች

* William Shakespeare (1564–1616) — ጸሐፊ፣ ተዋናይ — “የ Stratford ሊቅ”

* Anne Hathaway — የ Shakespeare ሚስት

* Hamnet Shakespeare — የ Shakespeare ልጅ — በ11 ዓመቱ ሞተ

* ኀምሌት (Hamlet) — የምድረ-ዴን ልዑል

* ገላውዴዎስ (Claudius) — ወንድሙን ገድሎ ዙፋን የያዘ ንጉሥ

* ገርትረድ (Gertrude) — ንግሥት — ኀምሌት እናት

* ወፌ-ይላ (Ophelia) — ኀምሌት ያፈቀራት

* ጶሎኔዎስ (Polonius) — አፈ-ንጉሥ

* ሆራትዮስ (Horatio) — ኀምሌት ወዳጅ

* ላርቆስ (Laertes) — ወፌ-ይላ ወንድም

* ፎርጠንብሮስ (Fortinbras) — የ Norway ልዑል

* Saxo Grammaticus — “Amleth” ታሪክን የጻፈ ዴንማርካዊ ታሪክ ጸሐፊ

ቦታዎች

* Stratford-upon-Avon — Shakespeare የተወለደበት

* Globe Theatre — London — ከ Thames ወንዝ ዳር ያለ ክብ ቲያትር ቤት

* Elsinore (Kronborg Castle) — ዴንማርክ — Hamlet ታሪኩ የሚካሄድበት ቤተ መንግሥት

* Wittenberg — Hamlet ያጠናበት ዩኒቨርሲቲ — Martin Luther ም ያጠናበት

ቃላትና ፅንሰ ሐሳቦች

* Elizabethan England — ንግሥት Elizabeth the First ዘመን (1558–1603)

* Renaissance — “ዳግም ልደት” — ከመካከለኛው ዘመን ማዕቀፍ ውጭ ማሰብ

* The Mousetrap — ኀምሌት ያዘጋጀው ተውኔት ውስጥ ተውኔት

* Revenge tragedy — የበቀል ተውኔት — በ Elizabethan ዘመን ታዋቂ ዘውግ

* Soliloquy — ገጸ ባሕሪ ለብቻው የሚያወራበት — “To be, or not to be” ታዋቂው



This is a public episode. If you would like to discuss this with other subscribers or get access to bonus episodes, visit www.zeresew.com
...more
View all episodesView all episodes
Download on the App Store

ZereSew ዘረ-ሰው PodcastBy ZereSew Team