ኢትዮጵያ በተያዘው ዓመት ሥራ ይጀምራል ተብሎ በሚጠበቀው የካፒታል ገበያ አገልግሎት ለሚያቀርቡ ድርጅቶች ፈቃድ ለመስጠት የምታደርገውን ዝግጅት እያጠናቀቀች ነው። የኢትዮጵያ ሴኪዩሪቲስ ኤክስቼንጅ ሥራ ለመጀመር የኢንቨስትመንት ባንኮችን ጨምሮ አስራ አምስት ዓይነት የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ይፈልጋል። እንደ ዋትስአፕ እና ቴሌግራም በመሳሰሉ መንገዶች የአክሲዮን ድርሻዎች በማሻሻጥ ሥራ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን አዲስ ፈቃድ መውሰድ አለባቸው።