ጌታ ወደ ህይወታችን ወደ ነገራችን የሚመጣው ለጥየቄያችንም መልስ የምናገኘው እኛ በፈለግነውና በራሳችነም እየተጋን ባለንበት ሳይሆን ነገር ግን በራሱ ጊዜና ሁኔታ ይመጣል:: በተለይ በራሳችን የሆነውን ጥረት ባቆምንና ረዳት በፈለግንበት ወቅት::
ጌታ ወደ እኛ ሲመጣ አይኖቻችንን ይገልጣል: :ለጌታ ያለን ፍቅር ይታደሳል:: ከለፋንለት ነገር ይልቅ የእርሱን ታላቅነትና ምሪት እናያለን:: በእርሱም በረከት እንሞላለን::
ጌታ በእኛ ህይወት ዋናው አላማ ፈፅመን እንከተለው ዘንድ ነው:: በዚህ ውስጥ :-
- ለጥያቄ መልስ ይገኛል::
- ከእርሱ ጋር ህብረት ማድረግ ይኖራል::
- እውነተኛ ፍቅር በተሞላን መጠንም እንዲሁ ጌታን ፈፅሞ መከተል ይሆንልናል::