የመጋቢት 11 ቀን 2016 ዓም ዐርዕስተ ዜና
የኢትዮጵያ የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል በአዲስ አበባ ከተማ እና በዙሪያዋ "በትጥቅ የታገዘ ሁከት እና ብጥብጥ ለመፈፀም በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ" ያላቸው 50 ሰዎች መያዛቸውን አስታወቀ።
የአማራ ክልል አሽከርካሪዎች በከፍተኛ የነዳጅ እጥረት ምክንያት ሥራችንን መስራት አልቻልንም ሲሉ ለዶቼቬለ ተናገሩ።የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ችግሩን ለመቀነስ ጥረት እየተደረገ ነው ብሏል።
የእስራኤል ጦር በጋዛው የአልሺፋ ሆስፒታል የነበሩ 90 ታጣቂዎች መግደሉን ዛሬ አስታወቀ። ሀማስ በሆስፒታሉ ውስጥ የተገደሉት ተዋጊዎች ሳይሆኑ ሰለማዊ ሰዎች ናቸው ሲል አስተባብሏል።