የመጋቢት 20 ቀን 2016 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
ለስምንት ወራት በእሥር ላይ የቆዩት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ክርስቲያን ታደለ እና የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል አቶ ዮሐንስ ቧያለው ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ።
ደቡብ ሱዳን በጎረቤት ሱዳን በሚካሄደው ጦርነት ምክንያት ዋነኛው የነዳጅ ዘይት ማስተላለፊያ መስመር መዘጋት የኤኮኖሚና የፖለቲካ ቀውስ እንዳያስከትልባት አስግቷል።
ሩስያ ትናንት ለሊቱን ዩክሬን በሚገኙ የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ላይ በፈጸመችው የአየር ጥቃት ሰበብ በሦስት ግዛቶች የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡን ዩክሬን አስታወቀች ።