አርስተ ዜና--የግሪክ ባህር ድንበር ላይ አንዲት ስደተኞችን የጫነች ጀልባ ተገልብጣ ሁለት ህጻናትን ጨምሮ የሰባት ሰዎች ህይወት አለፈ።--በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የኮሌራ በሽታ መከሰቱን የአማራ ክልል ህብረተሰብ ጤና ተቋም አስታወቀ። በቋራና በባህር ዳር ዙሪያ ወረዳዎች 1000 የሚጠጉ ሠዎች በበሽታው ተይጠዋል እስካሁን ዘጠኝ ሰዎች ሞተዋል።-- ትራምፕ ትዮጵያም ወደ አሜሪካ በምትልከዉ ሸቀጦች ላይ የ 10 በመቶ የቀረጥ ጭማሪ ጣሉ።--ዓለምአቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት የእስር ማዘዣ የቆረጠባቸዉ፣ የእስራኤሉ ጠ/ሚ ቤንያሚን ኔታንያሁ ያለምንም ችግር ቡዳፔስት ገቡ።