አርስተ ዜና፤
--በትግራይ ክልል የበረታው ውጥረት ጊዜያዊ አስተዳደሩን እና በፕሪቶሪያ የተፈረመውን የግጭት ማቆም ሥምምነት ከማፍረስ ባሻገር ጦርነት ሊቀሰቅስ እንደሚችል አቶጌታቸው ረዳ አስጠነቀቁ። በሌላ በኩል በዶክተር ደብረፅዮን የሚመራው የህወሓት ቡድን፥ ሦስተኛ ወገን ወደ ትግራይ እንዲገባ “ጥሪ መደረግ የለበትም” በማለት ተቃዉሞታል።
--በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መንግሥታት መካከል የተቀሰቀሰዉ ዉጥረት ለቀጠናዉ ሌላ ስጋት መፍጠሩን ሮይተርስ ዛሬ ዘገበ።
--የኮንጐ ሪፓብሊክ ባለሥልጣናት ከ M23 አማፂያን ለድርድር በሚቀጥለዉ ሳምንት ሉዋንዳ አንጎላ ላይ ለመገናኘት ተስማሙ።