በቤጂንግ የግማሽ ማራቶን ውድድር ቻይናዊ ሯጭን ሆን ብለው አሸናፊ አድርገውታል የተባሉት ኢትዮጵያዊ እና ኬንያዊ አትሌቶች እንዲሁም ቻይናዊዉ አትሌት የወሰዱትን ሜዳሊያና ሽልማት ተነጠቁ። ኬንያ የመከላከያ ኢታማዦር ሹሙን ጨምሮ ሌሎች ዘጠኝ ከፍተኛ መኮንኖች በሄሊኮፕተር አደጋ ከሞቱ። ዛሬ በሃገሪቱ የሦስት ቀናት ሃዘን ታወጇል። በ1 ሚሊየን የምርጫ ጣቢያዎች ድምጻቸውን የሚሰጡ ህንዳውያን ለስድስት ሳምንታት የሚዘልቀዉን ምርጫ ዛሬ ጀመሩ። አሜሪካ በተመድ የፀጥታ ም/ቤት ውስጥ ሙሉ አባል ለመሆን ፍልስጤም ያቀረበችዉን ማመልከቻ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብቷን ተጠቅማ ዉድቅ አደረገች።