አርስተ ዜና፤--የክርስቲያን ዴሞክራቶች ኅብረት ፓርቲ መሪ ፍሪድሬሽ ሜርስ አዲሱ የጀርመን መራኄ መንግሥት ሆኑ። ከሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት ወዲህ 10ኛዉ የጀርመን ቻንስለር ሜርስ ቃለ-መሃላ ፈፅመዉ ሥልጣኑን በይፋ ተረክበዋል።--በአማራ ክልል ከመተማ ጎንደር ያለው መንገድ ከተዘጋ አንድ ወር በማስቆጠሩ በአካባቢው ነዋሪዎች የማህበራዊና ኢኮኒሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ጫና ማሳደሩን ነዋሪዎች ተናገሩ።--ለሃገራት የሚሰጠዉ ሰብዓዊ እርዳታ መቀነስ በዓለም አቀፍ ደረጃ እድገት እንዲቀዛቀዝ ምክንያት ሆኗል ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።