አርስተ ዜና፤
--የአውሮጻ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሃላፊ ጆሴፍ ቦሬል በእስራኤል ሚኒስትሮች ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ሃሳብ ለማቅረብ እየሰሩ እንደሆነ ተመለከተ።
--በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጢ ዞን ጎርፍ ከ6ሺህ በላይ ነዋሪዎችን አፈናቀለ። የጎርፍ አደጋው መንሥኤ በአካባቢው ከተገነባ የመስኖ ግድብ ነዉ ተብሏል። በሌላ በኩል በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ በናዳ ለተጎዱ እርዳታ እየተጠበቀ ነዉ። --ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት «ሂውማን ራይትስ ዋች» በሱዳን ከ16 ወራት በላይ በዘለቀዉ የእርስ በእርስ ግጭት፤ ሁለቱንም ተፋላሚ ወገኖች ፤ የጦርነት ወንጀል ፈፅመዋል ሲል ከሰሰ።