አርስተ ዜናዎች፤
--የእስራኤል ጠ/ሚ ቤንያሚን ኔታንያሁ ለተጠረጠሩባቸው ክሶች የምስክር ቃላቸዉን ሰጡ። ኔታንያሁ ዛሬ በቴል አቪቭ በአንድ በህዝብ የተጨናነቀ ፍርድ ቤት በሰጡት የመክፈቻ ምስክርነት ቃል የእስራኤልን ጥቅሞች የሚጠብቁ ታማኝ መሪና ጠባቂ እንደሆኑ ገልፀዋል። የቀረበባቸዉ ክስ አገራቸዉን ሲከላከሉ ከገጠማቸዉ ተፈታታኝ ሁኔታዎች ጋር ሲነጻጸር፤ በውቅያኖሱ ውስጥ እንዳለ ጠብታ የሚታይ ነዉ ብለዉታል።
--የኬንያ ፖሊስ ዛሬ መዲና ናይሮቢ ላይ የሴቶች ግድያ እንዲቆም ሲሉ ለተቃዉሞ በወጡ ሰልፈኞች ላይ አስለቃሽ ጢስ ተኮሰ፤ ሦስት ሰዎችን አሰረዋል።
ሙሉዉን ዜና የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ!