የዓለም ዜና፤ የሐምሌ 9 ቀን 2016 ሰኞ
አርዕስተ ዜና
--የዩናይትድ ስቴትሱ ሪፐብሊካን ፓርቲ ዶናልድ ትራምፕን ለፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንዲፎካከሩ በይፋ መረጠ። ትራምፕ በበኩላቸዉ የአንድ ወቅት ተቃዋሚያቸውን ተጣማሪያቸው አድርገው መረጠዋል።
--በኬንያ ዛሬ ፕሬዝዳንት ሩቶ ስልጣን እንዲለቁ የሚጠይቁ ተቃዋሚ ሰልፈኞችን ዳግም ፖሊስ በአስለቃሽ ጢስ በተነ።
--በሩዋንዳዉ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ፤ ፖል ካጋሜ በከፍተኛ ድምጽ ማሸነፋቸውን የሃገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ይፋ ባደረገዉ የቅድመ ቆጠራ ዉጤት አስታወቀ።
--የሃንጋሪ ጠ/ሚ ቪክቶር ኦርባን የሚያደርጓቸውን አወዛጋቢ ጉዞዎች ተከትሎ የአዉሮጳ ህብረት ምክር ቤት እገዳ አስተላለፈ።