የአርብ መጋቢት 26 ቀን 2017 ዓም አርዕስተ ዜና
በአጭበርባሪዎች ተታለው ምያንማር የሄዱ ወጣት ኢትዮጵያውያን ዳግም የድረሱልን ጥሪ አቀረቡ።
ምሥራቅ ኮንጎ የሚንቀሳቀሰው M23 የተባለው አማጺ ቡድን ከስልታዊቷ ከተማ ዋሊካሌ ለቆ መውጣቱ ተሰማ። የኮንጎ መንግሥትና M23 የመጀመሪያውን ቀጥታ ንግግር ዶሀ ውስጥ የፊታችን ረቡዕ ሊካሂዱ ነው።
ቤጂንግ ለዩናይትድ ስቴትስ ታሪፍ የአጸፋ ምላሽ ሰጠች። ቻይና ከዩናይትድ ስቴትስ ወደ ሀገርዋ በሚገቡ እቃዎች ላይ ተጨማሪ የ34 በመቶ ታሪፍ መጣሏን ዛሬ አስታውቃለች። ካናዳን የመሳሰሉ ከፍተኛ ታሪፍ የተጣለባቸው ሀገራትም የአጸፋ እርምጃ ለመውሰድ እየተዘጋጁ ነው።