የዕለቱ መጽሄተ ዜና ትንታኔያችን በዋናነት የሚያተኩረው ኢትዮጵያ ውስጥ የጤና ባለሞያዎች ባነሷቸው ጥያቄዎች እና በመንግሥት ርምጃ ላይ ነው ። የቀጠለው የጤና ባለሙያዎች ጥያቄና የጤና ሚኒስቴር ምላሽ፤ ግቢ ልቀቁ የተባሉት ኢንተርን ሀኪሞች እና ሬዚደንቶች የተሰኙ ዘገባዎች እንዲሁም ሳምንታዊዎቹ አንድ ለአንድ እና ከወጣቶች ዓለም በጤና ባለሞያዎች ጥያቄ ላይ ያጠነጥናሉ ። በሕወሓት እና በፌዴራል መንግስት መካከል ስላለው ፍጥጫ የሚያወሳ ዘገባ፤ እና ስለ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የመካከለኛው ምሥራቅ ጉብኝት አንድምታም ቃለመጠይቅ አካተናል ።