የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትናንት የተወያየበት፣ የውጭ ዜጎችን የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት የሚያደርገው ረቂቅ ሕግ ላይ አዎንታም፣ አሉታዊም አስተያየቶች እየተሰጡ ነው።መቐለ የሚገኙ ፍርድቤቶች የስራ ማቆም አድማ፣ ዛሬም ቀጥሏል። በወሊሶ ከተማና አከባቢው ኤሌክትሪክ እና ውሃ ከተቋረጠ ሦስት ሳምንት ሊሆን ነው። እነዚህና የኢትዮ አሜሪካ ንግድ ምክር ቤት የፖሊሲ አስተያየትና የዕውቅና ሽልማት የዛሬው ዜና መጽሔት የሚመለከታቸው ጉዳዮች ናቸው