መገናኛ ብዙኃን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በመንግሥት ቁጥጥር ስር በሆነበት፤ አመጽና ዛቻን በመጋፈጥ፤ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. በሚካሄደው ምርጫ እንደሚሳተፉ ተዘገበ።
ዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ተልእኮ የወታደሮች ቁጥር በመቀሱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን አንድ ጥናት አመለከቱ።
ኢራን በመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነቱን ለማስቆም ከአሜሪካ ጋር የምታካሄደው ድርድር መሻሻሎች ቢኖሩትም ስምምነት ላይ ገና አልተደረሰም አለች። ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው ከኢራን ጋር የሚደረገው ስምምነት ወይ ታላቅና ትርጉም ያለው ይሆናል ወይ ደግሞ ስምምነት አይኖርም ብለዋል።