እስራኤል ትናንት ምሽት ራፋ ላይ ባካሄደችው የአየር ጥቃት ቢያንስ 35 ፍልስጤማውያን መገደላቸው ተሰማ። ጥቃቱ የተፈጸመው በጦርነቱ የተፈናቀሉ ወገኖች በተጠለሉበት ስፍራ መሆኑ ትኩረት ስቧል።
በእስራኤል እና ግብጽ አዋሳኝ ድንበር አካባቢ የተኩስ ልውውጥ አንድ የግብጽ ድንበር ጠባቂ ወታደር ተገደለ። ሁለቱም ሃገራት ጉዳዩን እየመረመሩ መሆኑን አስታውቀዋል።
ባለፈው ሳምንት ዓርብ በተከሰተ የመሬት መደርመስ ከሁለት ሺህ በላይ ሕዝብ ከእነሕይወቱ ሳይቀበሩ እንዳለቀረ የፓፓዋ ኒው ጊኒ መንግሥት አመለከተ።
የጀርመን ፍርድ ቤት ለሩሲያ በመሰለል በተጠረጠረ ወታደራዊ መኮንን ላይ የሦስት ዓመት ከመንፈቅ እስራት ፈረደ።