-ኢትዮጵያ ዉስጥ በኦሮሚያና አማራ ክልሎች የሚደረሱ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች አሁን አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ።።የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል በበኩሉ መንግስት የደነገገዉን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲያነሳ ጠይቋል።-ደቡብ አፍሪቃ ዉስጥ «ልዩ መራጮች» የተባሉ የሐገሪቱ ዜጎች ዛሬ ለሁለተኛ ቀን ድምፅ ሲሰጡ ዉለዋል።
-ስጳኝ፣ አየርላንድና ኖርዌ ዛሬ ለፍልስጤም በይፍ የመንግስትነት ዕዉቅና ሰጡ።እስራኤል ርምጃዉን አጥብቃ ተቃዉማዋለች።