የዜና መፅሔት ጥንቅራችን ኢትዮጵያና ኤርትራ ዳግም ጦርነት ይገጥሙ ይሆናል የሚለዉን ሥጋት ከምልክቶቹ ጋር ያሰባጠረዉን ዘገባ ያስቀድማል።አንድ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት በተፈናቃዮች አያያዝ ምክንያት የኢትዮጵያ መንግሥት ለመክሰስ ማቀዱን የሚዳስሰዉ ዘገባ ተከትሎ፣የኢትዮጵያ ዉስጥ ቴክኒክና ሙያ የሚያጠኑ ተማሪዎች ቁጥር ማሽቆልቆሉን የሚያወሳዉ ያሰልሳል።ዜና መፅሔቱ የጋምቤላ የወርቅ ምርት መጨመሩን የሚቃኝ ዘገባዉ አለዉ።