የዓለም ዜና

የሐምሌ 13 ቀን 2016 የዓለም ዜና


Listen Later

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) እንደ አዲስ ፓርቲ ለመመዝገብ ጥያቄ እንዳላቀረበ ቃል አቀባዩ አቶ አማኑኤል አሰፋ ተናገሩ። በአማራ ክልል የሚገኙ ሱዳናውያን ስደተኞችን ወደ ሌላ መጠለያ በማዘዋወር አውላላ እና ኩመር ጣቢያዎች በሒደት ሊዘጉ ነው። የኬንያ ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ የመንግሥታቸውን ካቢኔ አስራ አንድ አባላት ይፋ አደረጉ። ናይጄሪያ “በርካታ እና ተደጋጋሚ ጥፋቶች” ፈጽሟል ያለችውን የፌስቡክ እና የዋትስአፕ ባለቤት ሜታ ኩባንያ 220 ሚሊዮን ዶላር ቀጣች። የእስራኤል ኃይሎች ዛሬ ቅዳሜ በጋዛ ሠርጥ የተለያዩ አካባቢዎች በፈጸሟቸው ድብደባዎች ቢያንስ 30 ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የጤና ባለሥልጣናት አስታወቁ።
...more
View all episodesView all episodes
Download on the App Store

የዓለም ዜናBy DW