በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ከባድ ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ ከሐምሌ ወዲህ ቢያንስ በ125,000 ሰዎች ላይ ጉዳት አደረሰ። የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ማሕሙድ አሊ ይሱፍ የሊቢያን ቀውስ ለማብቃት የተባበሩት መንግሥታት ላዘጋጀው ፍኖተ-ካርታ ድጋፋቸውን ገለጹ። የየመን ጠቅላይ ሚኒስትር እና ሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናት በዚህ ሣምንት እስራኤል በፈጸመችው ጥቃት ተገደሉ። አሜሪካ በመስከረም በሚካሔደው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ የፍልስጤም አስተዳደር ፕሬዝደንት ማሕሙድ አባስ እንዲሳተፉ እንደማትፈቅድ አስታወቀች። የዩክሬን ምክር ቤት የቀድሞ አፈ-ጉባኤ አንድሬ ፓሩቢ በልቪቭ ከተማ በጥይት ተመተው ተገደሉ።