በሕገወጥ መንገድ የሚደረገው ስደት ዛሬም ቀጥሏል፤ በርካቶችም ሕይወታቸውን ማጣታቸው እየተነገረ ነው፤ የወጣት ኢትዮጵያዉያን አደገኛ የባሕር ላይ የስደት ጉዞ ማብቂያዉ የት ነዉ? የሚለው ቀዳሚው የምሽቱ የዜና መጽሔት ዘገባ ነው፤ በትግራይ ክልል ድርቅ የሰዎችን እንስሳትን ሕይወት መቅጠፉ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ለቀጠለው የጦርነት ስጋት የቀረቡ የመፍትሄ ሀሳቦች፤ የቀይ ባሕር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት አስቸኳይ ስብሰባ ፤ እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓመታዊ አፈጻጸም፤ ስኬትና እቅዶቹ የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል የዜና መጽሔት