Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
October 09የዜና መጽሔት፤ መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም አርብበዜና መጽሔት፤ የትግራይ ክልል ከተሞች ፀጥታ፤ተመድ ለኤርትራ ወረራ ምላሽ ይስጥ ስትል ኢትዮጵያ ጠየቀች ፤ሰሜን ወሎ በአፋር አማራ ድንበር ግጭት ተፈናቃዮች መጎዳታቸው፤ያገረሸው የኢትዮጵያ እና ኤርትራ መወነጃጀልንም የሚቃኝ የባልደረቦች ቃለምልልስ ይኖራል42 minPlay
October 07የመስከረም 27 ቀን 2019 የዜና መጽሔትበነገሌ ቦረና በተከሰተው ተኩስ የሰው ሕይወት ማለፉ፤በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ደጃች ሜዳ ወረዳ በወረዳው የተለያዩ ቀበሌዎች በድርቅ ምክንያት የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ምንም ዓይነት የምግብ ድጋፍ አልተደረገልንም ማለታቸውን፤ እንዲሁም የየመን ጦርነት የሚሉ ርዕሶችን ያስተነትናል።32 minPlay
October 06የመስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም. የዜና መጽሔትየኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ለምክር ቤቶች ያደረጉት የመርሕ ንግግር፤ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚደረገዉ ጦርነት፣ የሐገሪቱ የሰላም እጦትና የመሪዎችዋን ቃል በተመለከተ የሕዝብ አስተያዮቶች፤ መካነ-ሰላም ደቡብ ወሎ ዞን በመንግስት ጦርና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ከባድ ዉጊያ መደረጉ፤ ስለሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የተመድ፣ አሜሪካና የአዉሮጳ ሕብረት መልዕክቶች34 minPlay
October 05የመስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም የዜና መፅሔትየዜና መፅሄት ዝግጅታችን፤የቀጠለው የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት እና አዲስ የመንግስት ምስረታን፣ የፌደራል መንግስት ሀይሎች የተቆጣጠሩት የመቀሌ ከተማ የአመራር ለውጡን እንዴት እያስተናገደች ነው?፣በአማራ ክልል ሰቆጣ ከተማ የነበሩ የጻግብጅ እና አበርገሌ ወረዳ ተፈናቃዮች ወደቀያቸው መመለስ ጀመሩ መባሉን እንዲሁም የኤርትራ የሚሉ ዘገባዎች ተካቷል።21 minPlay
October 02የመስከረም 22 ቀን 2019 ዓ.ም የዜና መፅሄትበዛሬው የዜና መፅሄት አብዛኛ ጊዜን የሚሸፍነዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚደረገዉ ጦርነት፣ ኢትዮጵያ ከኤርትራና ግብፅ ጋር በገጠመችዉ ጠብ፣ የዲፕሎማሲ ግንኙነት የማቋረጥና ዲፕሎማቶችን የማባረርና አፀፋዉን የሚቃኙ ዘገባዎች ናቸዉ።አዲስ አበባ ፍንዳታ ከተሰማ ወዲሕ የሚደረገዉ የፀጥታ ቁጥጥርና የኢሬቻ በአል ዝግጅትን የሚቃኝ ዘገባና ቃለ ምልልስም ተካቷል።43 minPlay
October 01የመስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም. የዜና መጽሔትትላንት ምሽት በአዲስ አበባ በሦስት ቦታዎች ፍንዳታዎች እንደነበሩ መነገሩ፤ በትግራይ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች እየተደረገ የሚገኘው ውጊያ ወደ አዲስ አበባ ቀረበ ወይ የሚል ሥጋት አጭሯል፤እስራኤል ውጊያ እየተካሔደ ከሚገኝባቸው አካባቢዎች ዜጎቿን ማስወጣቷ ተሰምቷል፤ በጋዞ ዞን ዘጠኝ የፖሊስ አባላት ስለተገደሉበት ጥቃት የተዘጋጀ ዘገባም አለ።43 minPlay
September 30የመስከረም 20 ቀን 2019 የዜና መጽሔትየዜና መጽሔት፤ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የአካባቢውን ሃገራት እንዳያዳርስ ማስጋቱን፤ የኤርትራ ሠራዊት አፋር ውስጥ ገብቷል ስለሚለው የተደረገ ቃለ ምልልስ፣ መገናኛ ብዙኃን ኢትዮጵያ ውስጥ ስላገረሸው ጦርነት ምን ያህል መረጃ እየሰጡ ነው? ላሊበላ ያገረሸው ጦርነት ያስከተለባትን ስጋት የሚመለከቱ ዘገባዎችንም አካቷል፤22 minPlay
September 29የዕለተ ማክሰኞ መስከረም 19 ቀን፣ 2019 ዓ.ም ዜና መጽሔትየዜና መጽሔት ዝግጅታችን ሰሜን ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚደረገዉ ጦርነት በተፈናቃዮችና በየአካባቢዉ ሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ ያደረሰዉን ጉዳትና መከራን በሁለት ዘገቦች ይቃኛል። የኦሮሚያ ክልል 21 የአስተዳደር ዞኖችን ወደ 6 ዞኖች ማጠፉን የሚቃኘዉ ዘገባ አሠልሶ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 81ኛ ጉባኤና የድርጅቱ ፋይዳ ቢሲስነት በሚተነትነዉ ያሳርጋል።20 minPlay
September 28የመስከረም 18 ቀን፣ 2019 ዓ.ም የዜና መፅሄትበዛሬው የዜና መፅሄት በኢትዮጵያ ትግራይ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች በተቀሰቀሰው ውጊያ ላይ የጠናቀሩ ዘገባዎች ይቀርባሉ። የኦሮሚያ ምክር ቤት ዛሬ አዲስ ክልላዊ መንግሥት መሥርቷል። አቶ ሽመልስ አብዲሳ በፕሬዝደንትነት ሲቀጥሉ ስድስት ምክትሎች ተሾመውላቸዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ መጠናቀቅ የተመለከቱዘገባዎችም ተካተዋል20 minPlay