ዜና መጽሔት

ዜና መጽሔት

Download on the App Store

ዜና መጽሔት episodes

  • የቻይና እና አሜሪካ ኩባንያዎች ፉክክር በቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ
    የአሜሪካና ቻይና ኩባንያዎች ኢትዮጵያ በቢሾፍቱ ከተማ አቅራቢያ በምታስገነባው ግዙፍ አየር ማረፊያ ላይ ለመሳተፍ እየተፎካከሩ ነው ተብሏል። የቻይና ኩባንያዎች በግንባታ ውል ጨረታ በሰፊው እተሳተፉ ሲሆን፤ አሜሪካም ቦይንግን በመሳሰሉ ታላላቅ ኩባንያዎቿ በኩል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሚፈልገው ዘጠኝ ቢሊየን ዶላር ገደማ ውል ለመሳተፍ አቅደዋል።
    5 min
  • ባለፉት አምስት ወራት ብቻ 105 ስደተኞች መሞታቸው ተገለፀ
    ኢትዮጵያውያን በሚያዘወትሩት ምሥራቃዊ የፍልሰት መስመር ባለፉት አምስት ወራት ብቻ 106 ስደተኞች መሞታቸውን ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች መርጃ ድርጅት ገለፀ። እንደ ድርጅቱ ከአፍሪካ ቀንድ ተነስተው በጅቡቲና በቦሳሶ በኩል ወደ ባህረ ሰላጤው ሀገራት በሚደረጉ አደገኛ የስደት መስመሮች ከሚጓዙት 95 በመቶ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን ናቸው።
    5 min
  • ሲፒጄ በእሥር ላይ ያሉ 5 ጋዜጠኞች ይቅርታ ጠይቀው እንዲፈቱ ጫና ተደርጎባቸዋል አለ
    ኢትዮጵያ ውስጥ በእሥር ላይ ያሉ አምስት ጋዜጠኞች የተከሰሱበትን የሽብር ክስ አምነው ይቅርታ እንዲጠይቁ እና እንዲፈቱ ጫና እንደተደረገባቸው የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (ሲፒጄ) ገለፀ።ሲፒጄ በእሥር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ፣ገነት አስማው፣ዳዊት በጋሻው፣መስከረም አበራ እና አባይ ዘውዱ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጥሪ አድርጓል።
    4 min
  • የነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ/ም የዜና መጽሔት
    የጋዜጠኞች መብት ተማጋቹ ድርጅት ሲፒጄ የኢትዮጵያ መንግስት በጋዜጠኞች ላይ የሚደርሰውን ጫና ማውገዙ
    ኢትዮጵያውያን በሚያዘወትሩት ምሥራቃዊ የፍልሰት መስመር ባለፉት አምስት ወራት ብቻ 106 ስደተኞች መሞታቸውን የተባበሩት መንግሥታት የፍልሰተኞች መርጃ ድርጅት መግለፁን፣
    የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ድርጅት የዜጎች መብት እንዲከበር የሚቀርባቸው ሃሳቦች አለመተግበሩ እንዳሳሰበው መግለፁ
    በኢትዮጵያ በሴቶች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት ብሔራዊ ቀውስ ሆኖ እንዲታውጅ የመብት ተሟጋቾች ማሳሰባቸውን፣ እንዲሁም በኢትዮጵያ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ የቻይና እና የአሜሪካ ኩባንያዎች ፉክክርን ያስቃኛሉ።
    29 min
  • የሐሙስ ነሐሴ 7 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት
    የዜና መጽሔት፦ አፋር ክልል የተከሰተው የውኃ እጥረት ያስከተለው የእንስሳት ሞት፤ በዘንድሮው የክረምት ወቅት ዝናብ መቀነሱ፤ ሦስት የፖለቲካ ፓርቲዎች በምክክር ሂደቱ ላይ ያነሱት ሥጋት እና ያደረጉት ጥሪ፤ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ የተፈጸመ ግድያ እና የክልሉ የሰላምና የጸጥታ ቢሮ ያወጣው መግለጫ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ያጠላው የጦርነት ስጋት እና ውጥረት፤ እንዲሁም ኢትዮጵያና ሌሎችም ሃገራት ያወጣሁትን ወጭ ይክፈሉኝ ስትል ደቡብ አፍሪካ መጠየቋን የሚመለከቱ ዘገባዎችን አካትቷል ።
    30 min
  • የነሐሴ 6 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    የዜና መጽሔት ጥንቅራችን የኢትዮጵያ መንግሥት በአሸባሪነት ከከሳቸዉ ተጠርጣሪዎች 30 ያክሉ የተከሰሱበትን ወንጀል አምነዉ ምሕረት እንዲደረግላቸዉ የቀረበላቸዉን ጥያቄ ዉድቅ ማድረጋቸዉን የሚቃኘዉን ዘገባ ያስቀድማል። ዜና መፅሔቱ ምሥራቅ ወለጋ ዉስጥ የተጠናከረዉ ግጭት ሰዎች መጉዳትና ማፈናቀሉ፣ ከአማራ ክልል ከዋግኽምራ የተፈናቀሉ ሰዎች ርዳታ መማፀናቸዉ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ያጫረተዉን የዉጪ ምንዛሪ የሚያስተነትኑ ዘገቦች አሉት።
    19 min
  • የነሐሴ 5 ቀን 2018 የዜና መጽሔት
    በዜና መጽሔት አራት ዘገባዎችን እናስተነትናለን ። የሕወሓት ታጣቂዎች ላይ የተሰነዘረው የድሮን ጥቃት በአላማጣ፣ ለሰብአዊ መብት ሥጋት የደቀነ «የጦርነት አዝማሚያ» አለ መባሉ፤ በግልገል በለስ ከተማ በደረሰ ጥቃት ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸው እንዲሁም ኢትዮጵያውያን ለሶማሊያ ኅይሎች ያስረከቡት የስምሪት ቀጠና የሚሉ ዘገባዎችን ነው የምናስተነትነው ።
    17 min
  • የነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    የዜና መጽሔት
    ኢትዮጵያ እና ኤርትራ - እያደገ የመጣው ውጥረት፤ ከራያ አካባቢ በጦርነት ስጋት የወጣቶችና ሕጻናት በብዛት ለስደት መዳረግ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ድርቅ እና ግጭት ያጠላው ስጋት፤ እንዲሁም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አርሶአደሮች «የእርሻ ማዳበሪያ አልደረሰንም» ማለታቸው መገለጹ፤ የሚመለከቱ ዘገባዎችን አካቷል፤
    19 min
  • የነሐሴ 1 ቀን የዜና መጽሔት
    በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ላይ የሚሳተፉም የማይሳተፉም ፓርቲዎች ስለ ሂደቱ የሰጡት አስተያየት፣አሳሳቢው የሙስና አሻጥር በኢትዮጵያ ፣ "በስውር የአገር ማፍረስ ሴራዎች" ተጠርጥረው ዛሬ ፍ/ቤት የቀረቡ ፖለቲከኞች ለነሐሴ 11 መቀጠራቸው ፣ በጦርነት ትምህርታቸውን ያቋረጡ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ የሚደረግ ጥረት እንዲሁም ጥቂቶችን ተጠቃሚ ያደረገው የድሬዳዋ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ በዜና መጽሔት ዝግጅታችን ትንታኔ የሚቀርብባቸው ርዕሶች ናቸው።
    25 min
  • የሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    በዛሬው የዜና መጽሔታችን ስድስት ርዕሰ ጉዳዮችን በትንታኔ እናስደምጣለን ፤ ራያና እና አላማጣ አካባቢዎች ጦርነቱ ማየሉን እና ሴቶች ለቡድን ጾታዊ ጥቃት መዳረጋቸው ፤በሰሜን ኢትዮጵያ ያጠላው የጦርነት ስጋት ፤ ተጎጂዎች እና የአውሮጳ የሰላም ፋውንዴሽን ጥሪ ፤የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ሂደት እና የቀጣይ ሥራዎች ላይ ለዶቼ ቬለ የተሰጠ ምላሽ፤ የዐማራ ግሎባል ፎረም የምክክር ጉባኤውን መቃወሙ፤ ሲፒጄ ለ6 ሃገራት ጋዜጠኞች ሽልማት ሲሰጥ በኢትዮጵያ የታሠሩት እንዲፈቱ መጠየቁ፤ በሳዑዲ አረቢያ የሚመራው የ14 ሀገራት ቅንጅት በይፋ ከተገለጸው አላማ የሰፋ ትርጉም አለው መባሉ፤ በዝርዝር ይደመጣሉ።
    30 min

About ዜና መጽሔት

From the publisher's feed

በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ…