ዜና መጽሔት

ዜና መጽሔት

Download on the App Store

ዜና መጽሔት episodes

  • የነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም የዜና የዜና መፅሄት
    ከዓለም ዜና በኋላ በሚከተለው በዛሬው የዜና መጽሔት ጥንቅራችን፣የትግራይ ክልል ባለስልጣናት የአፍሪካ ህብረት ልዩ መልእክተኛ የመቀሌ ጉብኝት ያመጣው አዲስ ምክረሃሳብ የለም ማለታቸው፤በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ የኦባሳንጆን የመቀሌ ጉብኝት በበጎ እንደሚመለከተው መግለፁን፣ምሥራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ታጣቂዎች ትናንት ሰዎች ገድለው፤ ንብረት ስለማውደማቸው እንዲሁም በአላማጣ እና ዙሪያዋ የሚገኙ ነዋሪዎች ከባድ የእህል እና የገንዘብ መዋጮ በግዴታ እየተጠየቅን ነው ማለታቸውን የሚያስቃኙ አራት ርዕሰ ጉዳዮችን አካቷል።
    19 min
  • የነሐሴ 19 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መፅሔት
    የዜና መጽሔት ጥንቅራችን የዛሬዉ የመዉሊድ በዓል አከባበር በአዲስ አበባ ያልነዉን ርዕሥ ያስቀድማል። የአፍሪቃ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ ኦሌሴጎን ኦባሳንጆ የኢትዮጵያ መንግሥትና የህወሓት መሪዎችን እንደገና ለመሸምገል የጀመሩትን ዲፕሎሲ የሚቃኘዉ ዘገባ ተከትሎ፣ሥለ ዘንድሮዉ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዉጤት የተጠናቀረዉ ያሰልሳል።ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሰሞኑን በተከፈቱ ጥቃቶችና ግጭቶች የተፈናቀሉ ሰዎች ብዛትና ጥያቄን የሚዳስስ ዘገባም አለን።
    19 min
  • የነሐሴ 15 ቀን፣ 2018 ዓ.ም መጽሔተ ዜና
    ዜናውን በሚከተለው የዜና መጽሔት፤
    ሰሜን ወሎ በፀረ ተሽከርካሪ ቦምብ ፍንዳታ አራት ሰዎች መገደላቸው፤
    የመቀሌው የአየር ጥቃት ሰላባዎችና ነዋሪዎች አስተያየት
    በምክክሩ የጎላ መነጋገሪያ ሆኖ የቀጠለው የአዲስ አበባ ጉዳይ ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያቀረበው ከፍተኛ የዶላር ጨረታ እንዲሁም በአውሮጳ አትሌቲክስ ውድድር ለጀርመን ወርቅ ያስገኘው ትውልደ ኤርትራዊው ጀርመናዊ አማናል ጴጥሮስን የሚመለከቱ ዘገባዎችን አካቷል፤
    የዕለተ ዓርብ ሳምንታዊ መሰናዶ ከወጣቶች ዓለም፤ እንዲሁም የዚህ ሳምንት የዶቼ ቬለ እንወያይ የቅምሻ ጥንቅርም ይኖረናል።
    26 min
  • የነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    በዜና መጽሔት ፤
    ስለአገራዊው ምክክር የነዋሪዎች አስተያየት ፣ በትግራይ ክልል እየተፈፀሙ ያሉ የድሮን ጥቃቶች ፣ የምስራቅ ወለጋው የጊዳ አያና ጥቃትና የነዋሪዎች ተቃውሞ ፣ በደቡብ ወሎ 3,500 ያህል ከአረብ ሀገራት ተመላሾች በሀገራቸው የስራ እድል ማግኘታቸውን ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር አርማውን ያለ አግባብ የሚጠቀሙ እንዳሉ መግለጹን የተመለከቱ ዘገባዎች ተካተዋል።
    26 min
  • የነሐሴ 13 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    የዜና መጽሔት ጥንቅራችን የኢትዮጵያ የምክክር ጉባኤ የመጨረሻ ሰነድ ነገ ለተመካካሪዎች ይቀርባል ሥለመባሉ የተጠናቀረ ዘገባን ያስቀድማል።የዩናይትድ ስቴትስ ፍርድ ቤት አሜሪካ ዉስጥ በጊዚያዊነት እንዲኖሩ የተፈቀደላቸዉ ኢትዮጵያዉያን ፍቃድን ማቋረጡን የሚቃኘዉ ዘገባ ተከትሎ፣ በሰሜን ጎንደር ጠለምት ወረዳን ድርቅና ወረርሺኝ የሰዉና የእንስሳት ሕይወት ማጥፋታቸዉን የሚያወሳዉ ያሰልሳል።ዜና መፅሔቱ የኑሮ ዉድነት በቡሔ በዓል ላይ ያደረሰዉን ጫና የሚቃኝ ዘገባም አለዉ።
    19 min
  • የነሐሴ 12 ቀን 2018 የዜና መጽሔት
    ዜናዉን የሚለጥቀዉ የዜና መጽሔት ጥንቅራችን ፤ ማነጋገሩን የቀጠለው የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ግንኙነት ቀዳሚዉ ዘገባችን ነዉ። በምክክር ጉባኤው ከፍተኛ መነጋገርያ የሆነዉ የአዲስ አበባ ጉዳይ፤ ሌላዉ በስፋት የምናየዉ ጉዳይ ነዉ። ወጣቶችና ሴት ተፈናቃዮች ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸው እና ሴተኛ አዳሪነት የገቢ ምንጭ እየሆነ መምጣቱ ፤ አብዛኛዎቹ አፍሪካውያን ወጣቶች የተሰማሩት መደበኛ ባልኾኑ የስራ ዘርፎች መኾኑን የዓለሙ የስራ ድርጅት ማስታወቁ፤ እንዲሁም በናይል ውሃ አጠቃቀም የግብጽ ዛቻ የሚሉ ዘገቦችንም ዜና መጽሔት የአካተተዉ ርዕሰ ጉዳዮች ናቸዉ።
    23 min
  • የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ያጋጠመው ተግዳሮት
    የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም በአስተዳደር በደሎችና ቅሬታዎች ላይ የሚሰጣቸው ምክረ ሀሳቦች በአስፈፃሚዉ አካል እይተገበሩም ሲል አማረረ ፡፡ የተቋሙ የሥራ ሃላፊዎች እንደሚሉት አብዛኞቹ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች ለተቋሙ ጥያቄዎች ምላሽ ባለመስጠታቸውና ውሳኔውንም ባለመተግበራቸው ለዜጎች መብት ጥሰት ምክንያት እየሆኑ ይገኛሉ።
    4 min

About ዜና መጽሔት

From the publisher's feed

በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ…