Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
August 05የሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔትየዜና መጽሔት: ኢትዮጵያና ግብፅ በዓባይ ወንዝ ዉኃ አዘቃቀም ሰበብ የገጠሙት ዉዝግብ ሞቅ ቀዝቀዝ እንዳለ መቀጠሉን የሚቃኘዉን ዘገባ ያስቀድማል። ከወደ ሰሜን ኢትዮጵያ የጦርነት ሥጋት ባንዣበበት ባሁኑ ወቅት የደቡብ ወሎ ወጣቶች፣ የአቅመ-ደካሞችን ቤቶች መጠገንን ጨምሮ ለየአካባቢያቸዉ ሕዝብ 1.4 ቢሊዮን ብር የሚገመት ነፃ አገልግሎት መስጠታቸዉ ተዘግቧል።ለጋምቤላ በተለይ ለኑዌር ዞን የዘንድሮዉ ክረምት የድርቅ ሥጋት አስከትሏል።ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ የወባ በሽታ አለቅጥ ተዛምቷል።ጀርመን ለአፍሪቃ ሕብረት የሰጠችዉ የገንዘብ ድጋፍ የአፍሪቃ ሐገራትን ድንበሮች ለማካለል እየጠቀመ መሆኑ ከአዲስ አበባ ተሰምቷል።22 minPlay
August 04የሐምሌ 28 ቀን 2018 የዜና መጽሔትየኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ይስሐቅ ወልዳይ እንዲሁም የፓርቲው አባል ፖለቲከኛ አበበ አካሉ በመንግሥት የፀጥታ ኃይል መታሠራቸውን ፓርቲው ገለፀ።የሰሜን ኢትዮጵያው የጦርነት ስጋት ቀጠናዊ ስጋት ያጭር ይሆን?የሸረሪናው ውጊያ ያሰጋው የከባድ ጦርነት መጀመሪያ ይሆን? "በቀደመው የትግራይ ጦርነት የፍትህና ተጠያቂነት ማጣት ለቀጣይ ግጭት በር ከፍቷል " አምነስቲ22 minPlay
August 03የሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔትየዜና መጽሔት ዝግጅታችን ሰሞነኛው የግጭት መረጃ እና የመገናኛ ብዙኃን የይዘት አቀራረብ አንደምታ፤ በትግራይ ድንበር አካባቢ የተቀሰቀሰው ጦርነት በርካቶች ወደ ሱዳን እንዲሰደዱ ማስገደዱ፤ በቆቦ አካባቢ ወታደራዊ ዝግጅት መጠናከሩ እንዲሁም ሕይወት የቀጠፈ የመሬት መንሸራተት አደጋ በጻድቃኔማርያም ገዳም መከሰቱን የሚመለከቱ ዘገባዎችን አካቷል19 minPlay
July 31የሐምሌ 24 ቀን 2018 የዜና መጽሔትአንድ የጀርመን ተቋም በኢትዮጵያ ግጭት እንዳይከሰት የሰጠው ምክረ-ሐሳብ፤ ፌደራል ፖሊስ በደቡብ ኢትዮጵያ መስመር በሕገወጥ ሰዎችን የሚያሸጋግሩትን መቆጣጠሩን መግለጹ፤ የተማሩ ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን ኢላማ ያደረገው የኢንተርኔት ማጭበርበር፤ ዋግህምራ ዞን አበርገሌ እና ጻግብጂን የተቆጣጠረዉ ታጣቂ ቡድን ተዋጊዎችን እየመለመለ ነው መባሉ፣ መተከል ዞን ከጉባ-ግልገል በለስ የተበላሸው መንገድ፤ እንዲሄም ሮም ጣሊያን ላይ እየተካሄደ የሚገኘው በአውሮጳ የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል ድግስን የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል።28 minPlay
July 30የሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ/ም የዜና መጽሔት1, የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የመረጃ ተደራሽነት ላይ የተሰጡ አስተያየቶች 2, የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤና የሌሎች ሀገሮች ተሞክሮ 3, በትግራይ የተመናመነው ሰብዓዊ ድጋፍ እና የተፈናቃዮች እሮሮ 4, የአዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ በድሬደዋ 5, ጣና ሐይቅን እየፈተነ ያለዉ የእምቦጭ አረም //እንዲሁም6, አፍሪካ ኀብረት በሶማሊያ ያለው ሚና ወደ ፖለቲከዊ ተልዕኮ እንዲሸጋገር መጠየቁ27 minPlay
July 29የሐምሌ 22 ቀን 2018 የዜና መጽሔትበዜና መጽኄት አምስት ዘገባዎችን እናስተነትናለን ። ግድያና ጥቃትን የተመለከቱ የምርመራ ውጤቶች ትኩረት አግኝተዋልን? ሲል የሚጠይቀው ቀዳሚው ዘገባችን ነው ። ከ90 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች በ4 ጣቢያዎች ለብርቱ ዝናምና ጎርፍ ተጋልጠዋል መባሉ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዓመቱ ስኬቶች እና ያጋጠሙት ፈተናዎች፤ IOM ምስራቅ አፍሪቃውያን በዓለም አቀፍ ወንጀል እንዲሳተፉ እየተገደዱ ነው ማለቱ እንዲሁም የሰው ሠራሽ አደጋ በማጃንግ ዞን ጥብቅ ደን ላይ አደጋ ደቅኗል ይሰኛሉ ዘገባዎቹ21 minPlay
July 28የዜና መጽሔት፤ ሐምሌ 21 ቀን 2028 ዓ.ም ማክሰኞየዜና መጽሔት ጥንቅራችን ዩናይትድ ስቴትስና ኢትዮጵያ በጋራ ያዘጋጁትን ሲምፖዚየም አላማ ፤ትግራይ ክልል ለ2019 በጀት ዓመት 65 ቢሊዮን ብር ማፅደቁ ከመቀሌ ሲነገር፣ በክልሉ ይደረጋል ያሉትን ወታደራዊ ምልመላና ጦርነት ያሰጋቸዉ ወጣቶች በብዛት መሸሻቸዉ ከአማራ ክልል ተዘግቧል።የደቡብ ኢትዮጵያ አስተዳደር በአደጋ ለተፈናቀሉ ነዋሪዎች ቤት መስራቱ እንዲሁም የአፍሪቃ ሕብረት የዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮችን ስብሰባ በአዲስ አበባ የተሰኙ ዘገባዎችን አካቷል።23 minPlay
July 27የሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም የዜና መፅሄትየዛሬው የዜና መ።ፅሄት፤ ለአማራ እና ለትግራይ ምኁራን የቀረቡ የትብብር ጥሪዎችና ያላስማሙ ተቃርኖዎች፣በምስራቅ ወለጋ ዞን በታጣቂዎች የደረሰው ጥቃት፣የደቡብ አፍሪቃዉ መጤ ጠል ጥቃትሃገሪቱን ከአፍሪቃ ማቃረኑ እንዲሁም የኢትዮጵያ የፊልም ፌስቲቫል በፓሪስ የተሰኙ ርዕሶችን ያስተነትናል።19 minPlay
July 24የዕለተ ዐርብ ሐምሌ 17 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔትየዓለም ዜናን የሚከተለዉ የዜና መጽሔት፤ -በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ነው ያለው የዘር ማጥፋት እና የእርስ በርስ ጦርነት እንዲቆም፣ ሲል ጥሪ ያቀረበዉ የኢትዮጵያውያን ትብብር ንቅናቄ -በትግራይ ክልል እየተደረጉ ያሉ ሰሞነኛ ስብሰባዎችና የነዋሪዎች ኹኔታ - በቀይ ባሕር በሁቲ ታጣቂዎች የተፈፀ የመርከቦች ጥቃትን የአፍሪካ ኅብረት ማዉገዙ -የኢትዮጵያ የስደተኞች እና ተመላሾች አገልግሎትን ለማስተሳሰር ያለመ አዲስ ፍኖተ-ካርታ ይፋ መሆኑ - እንዲሁም ተግባራዊ የሆነው ተንቀሳቃሽ ማህበረሰብ አቀፍ የጤና ፕሮግራም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተሰኙ ርዕሶችን ይዟል።26 minPlay
July 23የሐምሌ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔትበዜና መጽኄት አምስት ዘገባዎችን እናስተነትናለን ። ዘገባዎቹ፦ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን፦ የምክክር ጉባኤ ተሳታፊዎች በሚያቀርቡት ሐሳብ እንዳይጠየቁ ኃላፊነት እወስዳለሁ ማለቱ፤ የድሮን ጥቃት በአባይ ገዳመ አስቄጤስ አቡነ አረጋዊ እና ቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም፣ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦነሰ) ከሌሎች ታጣቂዎች ጋር ስለመተባበር ምን አለ? ደቡብ አፍሪቃ፡ ኢትዮጵያውያን በፈቃደኝነት ወደ አገራቸው የተመለሱ ነዉ፤ እንዲሁም የአሜሪካ ሕግ አውጪ ምክር ቤት ስለ ኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት፤ ይሰኛሉ ዘገባዎቹ ።25 minPlay