ዜና መጽሔት

ዜና መጽሔት

Download on the App Store

ዜና መጽሔት episodes

  • የማክሰኞ ሰኔ 30 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት
    የዜና መጽሔት ጥንቅራችን፣ ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ለጦርነት እየተዘጋጀ ነዉ ሲሉ፣ -የዚያዉ ከትግራይ ክልል ወጣቶች ደግሞ አፈሳና የጦርነት ዝግጅት እንዳሳሰባቸዉ እያስታወቁ ነዉ።የዳግም ጦርነት ዝግጅት፣ ወቀሳና ሥጋቱን ዜና መጽሔቱ በሁለት ዘገቦች ያስተነትናል።የኢትዮጵያ ምርጫ የጥቃት ኢላማ እንደነበር፣ የሐገሪቱ ምጣኔ ሐብት ግን ዘንድሮም በ10.2 በመቶ አድጓል መባሉ ከወደ አዲስ አበባ ተሰምቷል።ሌላዉ የዜና መፅሔት ርዕስችን በሱዳንዋ ሥልታዊ ከተማ አል-ዑቤይድ የተፈፀመዉ የመብት ጥሰትና ይደርሳል የተባለዉ ተጨማሪ ጥፋት የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ኮሚሽንን እያባተለ መሆኑን ይቃኛል።
    21 min
  • DW Amharic የሰኔ 29 ቀን 2018 ዜና መጽሔት
    በአፍሪቃ ቀንድ እየጨመረ የመጣው የጦርነት ስጋት፣ የፀጥታ ሥጋት ያጋጠመው የጋሞ ዞን ዛይሴ አካባቢ፣ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ያልተቀመጠዉ የትግራይ ክልል ቅሬታ
    15 min
  • የሰኔ 26 ቀን 2018 የዜና መጽሔት
    እቅዱን አሳክቷል የተባለው የኢትዮጵያ የቡና ገቢ ፣ በአሜሪካ የትግራይ ማኅበረሰብ አባላት፣ስለትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ የሰጡት አስተያየት ፣በድሬደዋ የተማሪ ህፃናት ምገባን በተደራጃ መንገድ ማከናወን ያስችላል የተባለ ፕሮጀክት በይፋ መጀመሩ እንዲሁም የቀድሞ የኢራን ላዕላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሚኒ አስከሬን ሽኝት የተሰኙት ርዕሶች ይተነተናሉ።
    23 min
  • የሰኔ 25 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    የዜና መጽሔት ዝግጅታችን ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ታጣቂዎች 13 ሰዎች መግደላቸዉን የሚቃኝ ዘገባ ያስቀድማል።ዜና መፅሔቱ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ የኮሬ ዞን አስተማሪዎች ተማሪዎችን ላለመፈተን ማደማቸዉን ከዞኑ አስተዳደር መልስ ጋር ያሰባጠረ ዘገባም አለዉ።የአዉሮጳ የሙቀት መጠን ማየልና የፖለቲካዊ መርሕ ለዉጥ ጥያቄ፣ የቻይና ኮሚንስት ፓርቲ 105ኛ ዓመት በአል፣ የዓለም የእግር ኳስ ግጥሚያ የአፍሪቃ ቡድናት ሽንፈት ያልናቸዉንም ርዕሶች ያስተነትናል።
    27 min
  • የሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    የዜና መጽሔት፤
    አዲሱ የመኖሪያ ቤት የኪራይ ዋጋ ጥናት፤ በጋምቤላ ክልል ባህላዊ የግጭት አፈታት ዜዴዎች ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ስለሚኖራቸው ሚና፤ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና መጀመሩ እንዲሁም የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እዚያ ስለሚወለዱ ልጆች ዜግነት ያሳለፈው ውሳኔን የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል።
    19 min
  • የሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    የዜና መጽሔት ዝግጅታችን የኤርትራ የወደፊት ኅልዉና የፕሬዝደንቷ አገዛዝ ያልነዉን ርዕሥ ያስቀድማል። ዜና መፅሔቱ አዲስ አበባ ዉስጥ በተዘዋዋሪ አዉቶብሶች የዲጅታል የሕዝብ አገልግሎት መሰጠቱ፣ የደቡብ አፍሪቃ መጤ ጠል ቡድናት በከፈቱት ዘመቻ ላይ ሊነጋገር የነበረዉ የአፍሪቃ ሕብረት ስብሰባ መራዘምና የዓለም እግር ኳስ ዋንጫን የሚቃኙ ዘገቦችና ቃለ ምልልስን አካቷል።
    20 min
  • DW Amharic የሰኔ 22 ቀን 2018 ዜና መጽሔት
    የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድ የኢትዮጵያ ጉብኝት፣ በትግራይ የወጣቶች አፈሳ ቀጥሏል መባሉና የአውሮፓ ህብረት ማስጠንቀቂያ፣ የቀነ ገደቡ መጠናቀቅ እና የፍልሰተኞች ሥጋት በደቡብ አፍሪካ
    20 min
  • የዓርብ ሰኔ 19 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት
    ዜናዉን የሚለጥቀዉ የዜና መፅሔት ዝግጅታችን ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አዲስ የደነገገዉን ሕግ እንዲሽር ሑማን ራይትስ ዋች ያቀረበዉን ጥያቄ ህወሃት ዉድማድረጉን የሚተነትነዉን ዘገባ ያስቀድማል።ዜና መፅሔቱ፣ የጋቤላ ብልፅግና ፓርቲ ፅሕፈት ቤት ከተቃዋሚዎች ጋር ተባብሮ ለመሥራት ቃል መግባቱ፣ ደቡብ አፍሪቃ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ጥቃት ይደርስብናል የሚለዉ ሥጋታቸዉ መናሩ፣ የመረጃ ጥቅም፣ የአፍሪቃ አቅምና ዝግጅት፣ እንዲሁም የዓለም የእግር ኳስ የዋንጫ ግጥሚያን የሚቃኙ ዘገቦችና አጭር ዉይይቶች አሉት።
    26 min
  • የሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ለምክክር ጉባኤ የመረጣቸው ስምንቱ አጀንዳዎች፤ በአስተያየት ሰጪዎች ተስፋ እና ሥጋት የተንጸባረቀበት አገራዊ ምክክር፤ የኦሮሚያ ክልሉ ግጭት እና ዘላቂ መፍትሄው፤ የኢቦላ ስርጭትን ለመከላከል የጉዞ እገዳ አስፈላጊ አይደለም ሲል ዐአፍሪካ ሲዲሲ ዐሳወቀ፤ በስፔን ከ200 በላይ ሰዎችን የገደለው የሙቀት ወጀብ በፈረንሣይስ ምን አደረሰ?
    25 min

About ዜና መጽሔት

From the publisher's feed

በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ…