ዜና መጽሔት

ዜና መጽሔት

Download on the App Store

ዜና መጽሔት episodes

  • የሰኔ 17 ቀን 2018 የዜና መፅሔት
    በዛሬው የዜና መፅሔታችን 4 ርዕሰጉዳዮች ይደመጣሉ።
    በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምሥራቅ ጉራጌ ዞን ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ሦስት የፀጥታ አባላት መገደላቸውን፤
    የትግራይ ጊዚያዊ መስተዳደር ያረቀቀው አስገዳጅ ወታደራዊ ምልመልን እንዲሰርዝ ሂዩማን ራይትስ ዎች መጠየቁን
    ከተመራጬ መንግስት ምን ይጠበቃል? በሚል መራጮች የሰጡት አስተያየት እንዲሁም
    የ12 ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን የሚመለከቱ ናቸው በዚሁ ቅደም ተከተል ይደመጣሉ።
    18 min
  • የሰኔ 16 ቀን 2018 የዜና መጽሔት
    የዜና መፅሔት ዝግጅታችን ኢትዮጵያ ዉስጥ የተደረገዉን ምርጫ ዉጤት በተመለከተ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሰጡት፣ ድጋፍ፣ ተቃዉሞና ምክርን በሁለት ዘገቦች እንቃኛለን።ከምርጫ ጋር የተያያዘ ነዉ በተባለ ጥራሬ አንድ የቀድሞ ዕጩ መታሰራቸዉን የሚያወሳ ዘገባም ሌላዉ ምርጫነክ ዘገባችን ነዉ።ዜና መፅሔቱ የህወሓት ታጣቂዎች አፋር ክልልን ማጥቃት ሰዎች መግደልና ማቁሰላቸዉንና የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የሚሰራጩ የጥላቻ ንግግሮችን መዘዝ የሚቃኝ ዘገባም አለዉ።
    25 min
  • የሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ/ም የዜና መፅሔት
    መጽሄተ ዜናችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ትናንት እሁድ ይፋ ባደረገው 7ኛ ው ጠቅላላ ሃገራዊ የምርጫ ዉጤት ላይ ያተኩራል። በቅርቡ ከኢትዮጵያ የተባረረችው ፈረሳያዊቷ ጋዜጠኛን አስመልክቶ ቀጣሪዋ ላክሮዋ ጋዜጣ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ያቀረበው ወቀሳም በዝርዝር ከሚደመጡ ዘገባዎቻችን አንዱ ነው።
    18 min
  • የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተጨማሪ ውጤቶችን ይፋ አደረገ
    ምርጫ ቦርድ ትናንት ዓርብ ማምሻውን በሰጠው መግለጫ ተጨማሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የክልል ምክር ቤቶች እጩ አሸናፊዎችን ይፋ አድርጓል፡፡ቦርዱ ይፋ ካደረጋቸው ውጤቶች መካከል የአብን ሊቀመንበር ዶ/ር በለጠ ሞላ እንዲሁም የቀድሞ የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ቀጄላ መርዳሳ በግላቸው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወንበር አሸንፈዋል።
    4 min
  • DW Amharic የሰኔ 12 ቀን 2018 የዜና መጽሔት
    በሰኔ 12 ቀን 2018 የዜና መጽሔት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ “አክራሪ” ባሏቸው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አባላትና በቤተሰቦቻቸው ላይ የጣሉትን የቪዛ ገደብ የተመለከቱ ሁለት ዘገባዎች ተካተዋል። የውክልና መቀመጫ ያገኙ ፓርቲዎች ቀጣይ መንገድ፣ ሥመ-ጥሩው የሙዚቃ ባለሙያ አዲስ ገሠሠ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፣ ኢትዮጵያ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ሰበብ ከአሜሪካ የሚመጣውን ጫና እንዴት ልትይዝ ይገባል? የሚሉ ዘገባዎችም ይቀርባሉ።
    24 min
  • የሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    የዜና መጽሔት ዝግጅታችን ኢትዮጵያን ወደ ባሕር በር መመለስ በአፍሪካ ቀንድ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና የደህንነት ትብብርን ያጠናክራል መባሉ፤ የተቃዋሚ ፓርቲ እጩዎች ቁጥር ሻል ብሎ የታየበት የምርጫ ውጤት፤
    መሶብ» የሚል መጠሪያ የተሰጠው የአንድ ማዕከል አገልግሎት፤ በጥብቅ የመንግሥት ቁጥጥር የሚመራው የቤት ኪራይና ዳራው፤ እንዲሁም የክረምት ወራት የአየር ጠባይ ሁኔታ ትንበያን የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል።
    26 min
  • የሰኔ 10 ቀን 2018 የዜና መጽሔት
    አሳሳቢው የጦርነት ስጋት በሰሜን ኢትዮጵያ ፣የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ «የቁጫ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ»ን አቤቱታ ውድቅ ማድረጉ፣ ዩናይትድ ስቴትሰና ኢራን ደረሱበት የተባለው ስምምነት አፍሪካን እንዳያዘናጋ ተንታኛች ማሳሰባቸው እንዲሁም ትራምፕን ጨምሮ የቡድን ሰባት አባል ሀገራት መሪዎች ዩክሬንን ለመደገፍ መስማማታቸው የዛሬው የዜና መጽሔት ዝግጅታችን የሚያተኩርባቸው ጉዳዮች ናቸው
    22 min
  • የጋዜጠኛ ሳልሳዊት ባይነሳኝ እስር
    ጋዜጠኛ ሳልሳዊት ባይነሳኝ ከሳምንት በፊት በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሏን ቤተሰቦቿ ለዶቼ ቬለ ገልፀዋል።የጋዜጠኛዋ ታናሽ እህት ለዶይቸ ቬለ እንደገለፀችው፤ እህቷ ያለፈው ሰኞ ሰኔ አንድ ቀን፣ 2018 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ አዲስ አበባ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቷ በፖሊስ ለጥያቄ ትፈለጊያለሽ ተብላ ነው የተያዘችው። ያም ሆኖ እስካሁን ፍርድ ቤት አልቀረበችም።
    5 min
  • የሰኔ 9ቀን 2018 የዜና መፅሔት
    የዜና መፅሔት ዝግጅታችን ኢትዮጵያ ዉስጥ የኑሮ ዉድነት በደሞዝተኞች ላይ ያሳረፈዉን ጫና ችግር የሚቃኘዉን ዘገባ ያስቀድማል።በትግራይ ክልል አዲስ የወጣዉ የወታደራዊ አገልግሎት ሕግ ያስከተለዉ ተቃዉሞና ሥጋት፣ ኢትዮጵያዊት ጋዜጠኛ መታሰሯና የአፍሪቃ ሕብረት ደቡብ አፍሪቃ ዉስጥ በተቀጣጠለዉ የዉጪ ጠል ጥቃትና ዛቻ ላይ ሊነጋገር ማቀዱን ዜና መፅሔቱ በየተራ ይተነትናል።
    20 min
  • DW Amharic የሰኔ 08 ቀን 2018 የዜና መጽሔት
    በሰኔ 08 ቀን 2018 የዜና መጽሔት የቱለማ አባገዳ ሥልጣን ሽግግር እና የቀጣዩ አባገዳ ፈተና፣ የኢራን አሜሪካ ስምምነት እንዲሁም የጡት ወተት ባንክ ምንድን ነው? የሚሉ ርዕሰ-ጉዳዮች ተካተዋል።
    17 min

About ዜና መጽሔት

From the publisher's feed

በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ…