ዜና መጽሔት

ዜና መጽሔት

Download on the App Store

ዜና መጽሔት episodes

  • የግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    አርዕስተ ዜና
    ሰባተኛው ዙር የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ መራጮች ዛሬ ለፌደራል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ለክልል ምክር ቤት ለሚወዳደሩ እጩዎች ድምጽ ሲሰጡ ውለዋል። የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኦሮሚያ ክልል በበሻሻ ከተማ የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሔር ታዬ ዐፅቀ ሥላሴ ደግሞ በአዲስ አበባ ዛሬ ጠዋት ድምጽ ሰጥተዋል።
    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ “በጸጥታ ምክንያት ወደ 143 የሚሆኑ የምርጫ ጣቢያዎች ” አለመከፈታቸውን ዛሬ አስታወቀ። የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላተ ወርቅ ኃይሉ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ የተወሰኑ የምርጫ ክልሎች የድምጽ አሰጣጥ ከተጀመረ በኋላ በጸጥታ ችግር መቋረጡን ተናግረዋል።
    13 min
  • የግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ጎሀፅዮን አካባቢ፤ ከአዲስ አበባ ወደ አማራ ክልል የጓሚዙ 12 መንገደኞች መገደላቸውን
    መጭው ምርጫ ከተሳታፊ ፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከታዛቢዎች እና ከመራጮች አንፃር
    በአማራ ክልል አሽከርካሪዎች በክልሉ ባለው ግጭት ሳቢያ ግድያ እና ዝርፊያ እየደረሰብን ነው ማለታቸው
    በደቡብ አፍሪቃ የሚታየውን የመጤ ጠል ጥቃት የሚያስቃኙ አራት ዘገባዎችን አካቷል።
    31 min
  • DW Amharic የግንቦት 20 ቀን 2018 የዜና መጽሔት
    የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ማስጠንቀቂያና የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ምላሽ፣ የሰባተኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ድባብ በአዲስ አበባ፣ ''ምርጫው፣ አገሪቱን ወደ ባሰ ቀውስ ሊያሸጋግር የሚችል ነው።''የጋራ-መድረክ፣ ምርጫና የሴቶች ተሳትፎ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣
    30 min
  • የረቡዕ ግንቦት 19 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት
    የዓለም ዜናን የሚከተለው የዜና መጽሔት፤ አዲስ አበባን ጨምሮ ከተለያዩ አካባቢዎች የደረሱንን የኢድ አል አድሀን በዓል የተመለከቱ ዘገባዎች ያስቀድማል፤
    የመጨረሻው የምርጫ ቅስቀሳ እና የፓርቲዎች አስተያየት፤ እንዲሁም የአፍሪቃ ሕብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን አዲስ አበባ መግባቱን የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል።
    በትግራይ ክልል “የወጣቶች የግዳጅ ምልመላ” እየተደረገ መሆኑ መገለጹ፤ በተጨማሪም
    የትግራይ ክልልን ወቅታዊ ሁኔታ በሚመለከት ከህወሃት ቃል አቀባይ ጋር አጭር ቃለ ምልልስ አድርገናል።
    34 min
  • የግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    በዜና መጽሔት አምስት ዘገባዎችን እናስተነትናለን ። በአማራ 8፣ በትግራይ 38 ምርጫ ክልሎች ላይ ግንቦት 24 ምርጫ አይደረግም መባሉ፤ የተፎካካሪ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳ በአማራ ክልል፤ የምርጫ ቅስቀሳቃ እና ፖለቲካ ፓርቲዎች አስተያየት፤ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የምርጫ ዘመቻ እንዲሁም የአፍሪቃ ኅብረት ባልተጠናቀቁ የቤት ስራዎቹ ላይ ማተኮር እንዳለበት ተገለፀ በሚሉ ርዕሶች ስር ተጠናቅረዋል።
    33 min
  • የግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    በፓርቲው ምክትል ሊቀ መንበር የሚመራው የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ ክፋይ ምርጫ ቦርድ "የዜጎችን መሠረታዊ የሰብአዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ሊነጥቅ አይገባም" ሲል ማሳሰቡን፤ የጎጎት ለጉራጌ አንድነት እና ፍትህ ፓርቲ በምርጫ ቅስቀሳ ላይ " ስልታዊ የሆኑ የምርጫ ሕግ ጥሰቶች ካልታረሙ ከምርጫው እራሱን ለማግለል እንደሚገደድ ማሳወቁን፤ በትግራይ ስላለው የጦርነት ድባብ የባለሙያ አስተያየት
    19 min
  • የዜና መጽሔት፤ ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ.ም
    የዜና መጽሔት-1-በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ዝግጅት- 2-ራሳቸውን ከምርጫ ያገለሉ የድሪዳዋ ከተማ እጩ ተወዳዳሪና ሐረሪ ክልል የሚንቀሳሱ ሌላ እጩ ተወዳዳሪ ስለ ምርጫው ሂደት የሰጡት አስተያየት
    3 -የንግድ ሱቆቻቸው የፈረሱባቸው ደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሮሮ-4-ወደ ውጭ የሚላክ የኢትዮጵያ ቡና ላይ የተጋረጠው ፈተና - 5 ቻይና በዓለም ኃያላን ተፈላጊ የሆነችበት ምክንያት በሚሉ ርዕሶች ስር የተቀናበሩ ዘገባዎች ይቀርቡበታል ሳምንታዊው ከወጣቶች ዓለም ከምርጫ 2018፤ ወጣቱ በርግጥ ምን ይፈልጋል?- በሚል ርዕስ ጋር ከተቀናበረ ዝግጅት ጋር ይጠብቀናል ።
    25 min
  • የግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    የዜና መጽሔት፤ ምርጫ ቦርድ ያሰማራው የፀጥታ ኹኔታን የቃኘው ቡድን ያቀረበው ውጤትና የፓርቲዎች አስተያየትን ያስቀድማል፤
    በምርጫ 2018 እና የተቀዛቀዘው የኦፌኮ ተሳትፎ፤ የደቡብ ወሎ የምርጫ ካርድ ውዝግብ
    ታግተው የነበሩ ከመቶ በላይ የፍንጫ ስኳር ፋብሪካ ጊዜያዊ ሠራተኞች መለቀቀቅ፤ የብሔራዊ ባንክ የ500 ሚሊዮን ዶላር ጨረታ እና የኑሮ ውድነት ስጋት እንዲሁም አፍሪካ ሲዲሲ ኢቦላ አስቸኳይ የኅብረተሰብ ጤና አደጋ ነው ማለቱን የሚስቃኙ ስድስት አካቷል።
    27 min
  • የግንቦት 12 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    በዜና መጽሔት አራት ዘገባዎችን እናስተነትናለን ። በሰሜን ወሎ ዞን ነዋሪዎች ለቀጣዩ ምርጫ «እንኳን ሌላ ፓርቲ ብልጽግናም ራሱ አይቀሰቅስም» ማለታቸው፤ ጠ/ሚ ዐቢይ ስለ ሥራና ሠራተኛ ባሰሙት ንግግር የሰዎች አስተያየት፤ የሁለት ዓመት አስገዳጁ የቤት ኪራይ ውል አዋጅ ሊያበቃ መቃረቡ፤ እንዲሁም የሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ (ሲፌፓ) በምርጫ ቦርድ ላይ ክስ መመሠረቱ ይሰኛሉ ዘገባዎቹ ።
    17 min

About ዜና መጽሔት

From the publisher's feed

በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ…